Your cart is currently empty!
በባሌ ዞን በአጋርፋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች የሚያገለግሉ ፈርኒቸር እና የቢሮ እቃዎች፣ የአዳራሽ ወንበር እና ጠረጴዛ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 24, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በባሌ ዞን በአጋርፋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች የሚያገለግሉ ፈርኒቸር እና የቢሮ እቃዎች ፣የአዳራሽ ወንበር እና ጠረጴዛ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ቀጥሎ የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችን እንዲወዳደሩ እንጋብዛለን።
1- ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል የሚያስችል በሚወዳደሩበት ዘርፍ የተሰማሩበት ህጋዊ የንግድ ፊቃድ ያላቸው ፤ የ2018 ግብር የከፈሉ /ያሳደሱና/ በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ(ቫት) ተመዝጋቢ የግብር ከፋይ ቲን እና በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
3- ተጫራቾች ለጫረታ ማስከበሪያ 30,000.00(ሰላሳ ሺ)ብር የያዘ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
4- ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን ሰነዶች ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
5- አቅራቢው ድርጅት ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለፀለት ከ5ኛው ቀን በኃላ ከ6ኛው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ መ/ቤት ቀርቦ ውል መፈራረም ይኖርበታል።
6- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 በአጋርፋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በተከፈተው የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000078933708 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በማስገባት ሰነዱን አጋርፋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ፡
7- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰኣት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
8- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0912 82 25 79 / 09 12 82 28 08 ደውለው ይጠይቁ።
ባሌ ዞን አጋርፋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት