Your cart is currently empty!
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ የአየር ንብረት አፈጻጸም የመሬት አያያዝ ፕሮግራም (CALM) አገልግሎት የሚውል የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ ባለ 10፣ ባለ14 እና ባለ 20ሚሜ እና የውሃ ማጠጫ ጆርዲን እንዲሁም የእጅ ጋሪ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጀት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 24, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ የአየር ንብረት አፈጻጸም የመሬት አያያዝ ፕሮግራም (CALM) አገልግሎት የሚውል
- ሎት 01 የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ ባለ 10፣ ባለ14 እና ባለ 20ሚሜ እና የውሃ ማጠጫ ጆርዲን እንዲሁም
- ሎት 02 የእጅ ጋሪ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጀት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራች ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
1. በዘርፉ የተሰማሩ እና በዘመኑ ስለመታደሱ የሚገልጽ እና ግብር የከፈሉበትን ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላችሁ።
3. የግዥው መጠን ብር 200,000 00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከኦርጂናሉ ጋር በማገናዘብ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. የሚገዙ የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ፣ ጆርዲን እና የእጅ ጋሪ ግዥ ዝርዝር መግለጫ | ስፔስፊኬሽን/ እና መቅረብ ያለባቸው አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 14 ማግኘት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ብር ጠቅላላ የዕቃ የግንባታ ወይም የአገልግሎት ዋጋ ብር በቁጥር ለሎት 01 ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺ ብር) እንዲሁም ለሎት 02. ብር 100,000.00/አንድ መቶ ሺ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) እና በቅድመ ሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ብቻ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው። ማንኛውም ተጫራች የጨረታ የመወዳደሪያ ሃሳቡን የቴክኒካል ሰነድ ዋና እና ቅጂ የብቻው እና የፋይናሽያል ሰነዱን እና የጨረታ ማስከበሪያን በአንድ ዋና እና ቅጅ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግብርና ቢሮ ግቢ ቢሮ ቁጥር 025 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገዛት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ለተጠየቁት ግዥዎች ናሙናቸውን ከቴክኒካል ሰነዱ ጋር አብረው ማቅረብ አለባችሁ።
8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግብርና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ 16ኛ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈለጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 25 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 5849/058 320 8095/ በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
11. ተጫራቾች ያለምንም ስርዝ ድልዝ የተሞላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ይህ ካልሆነ ሰነዱ ተቀባይነት ላይኖረው ይችላል፡፡ ባጋጣሚ የተሰረዘም ከሆነ የሞላው ድርጅት ፊርማ መኖር አለበት።
12. በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ