Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የእርዳታና የልማት ማህበር የተለያዩ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 24, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የእርዳታና የልማት ማህበር ሀገር በቀል የእርዳታና የልማት ማህበር ሲሆን ከ Norwegian Church Aid (NCA) ባገኘው ድጋፍ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ነንሰቦ እና ኮኮሳ ወረዳ እና በአማራ ክልል ኦሮሞ ልዩ ዞን ደዋጨፋ፤ አርጡማ ፉርሲ እና ጅሌ ጡሙጋ የሰላም ፕሮጀክቶችን እየተገበረ ይገኛል፡፡
ፕሮጅክቱን በሚተገብርባቸው አካባቢዎች ለወጣቶችና ሴቶችን የስራ እድል ለመፍጠር ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የወንዶች ፀጉር ቤት ዕቃ፣ የልብስ ስፌት ማሽን እና ጥቃቅን እቃዎች፣ TV, DSTV decoder; የካፌ ማሸን እና እንቁላል ጣይ ዶሮዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
አይነት እና ዝርዝር ሁኔታ |
መለኪያ |
ብዛት |
|
1 |
የወንዶች ፀጉር ቤት ዕቃዎች |
ቁጥር |
6 |
|
2 |
የልብስ ስፌት ማሽን እና ዕቃዎች |
ቁጥር |
3 |
|
3 |
የሻይ ማሽን |
ቁጥር |
2 |
|
4 |
72 ኢንች ቴሌቪዥን እና DSTV decoder |
ቁጥር |
2 |
|
5 |
ክትባት የጨረሱ የ 120 ቀን Sasso እንቁላል ጣይ ዶሮ |
ቁጥር |
200 |
|
6 |
ጄኔረተር |
ቁጥር |
2 |
|
7 |
የቢሮ አዳራሽ 24 ወንበር እስከ ጠረጴዛ |
ቁጥር |
1 |
በዚህም መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያለው ድርጅት ግለሰብ
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፡፡
2. ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ በኢትዮጵያ ሙስሊሞች የእርዳታና የልማት ማህበር ዋና ቢሮ በመገኘት የማይመለስ 200 ብር በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች ጨረታውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በአዲስ አበባ አየርጤና አካባቢ ወረዳ 05 ኮልፌ . ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በሚገኘው በኢትዮጵያ ሙስሊሞች የዕርዳታ እና የልማት ማህበር ቢሮ እስከ ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም 4:30 ሰአት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 7 ፐርሰንት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በኢትዮጵያ ሙስሊሞች የእርዳታና የልማት ማህበር ስም አሰርተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5. የጨረታ አሸናፊ ጨረታ ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውስጥ ውል በመፈፀም በ7 ቀናት ማቅረብ ግዴታ ይሆንበታል፡፡
6. ጨረታ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥቅምት 20/ 2018 ዓ.ም በ5፡00 ሰዓት በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ይከፈታል
7. የዶሮዎች ዋጋ እስከ አማራ ክልል ኦሮሞ ልዩ ዞን ደዋጨፋ እና አርጡማ ፉርሲ ወረዳ ድረስ የትራንስፖርት ዋጋን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
8. መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር +2511 348 2463, 0921 019 298, 0929 187 182
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የእርዳታና የልማት ማህበር