Your cart is currently empty!
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በ2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን የሥራ መገልገያዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 25, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን የሥራ መገልገያዎች ሎት አንድ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ ሎት ሁለት ልዩ ልዩ መሣሪያዎች፣ ሎት ሶስት አላቂ የፅዳት እቃዎች፣ ሎት አራት ህትመት፣ ሎት አምስት ቋሚ እቃዎች (ups፣ ቴሌቨዥን እንዲሁም ቴሌቨዥን ማስቀመጫ ሌሎችን)፣ ሎት ስድስት የደንብ ልብስ የአደጋ መከላከያና የጤና መጠበቂያ እቃዎች፣ ሎት ሰባት የፕሪንተር የፎቶ ኮፒ እና የጄኔሬተር ሰርቪስና ጥገና፣ ሎት ስምንት የመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ /ግማሽ ሌትር ውሃ እና ቆሎ/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግና የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች በጨረታው መወዳደር ይችላል።
- የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ እና መረጃውን ማቅረብ የሚችል።
- ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠማስረጃ ማቅረብ።
- ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት።
- ማንኛውም ተጫራች 200 /የሁለት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥራችን 1000383805035 በማስገባት እስሊፑን ይዘው የጨረታውን ሰነድ በሥራ ሰዓት ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሲኤምሲ ሚካኤል ፊት ለፊት ድልድዩ አጠገብ ዴሉክስ ፈርኒቸር ጀርባ ያለው ህንጻ 4ኛ ፎቅ ግዥና ፋይናንስ ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሠረት ዋናውንና ኮፒውን የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ፖሰታ በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር /10/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀንን ጨምሮ በተጠቀሰው ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላውን ዋጋ 2% በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሚል ስም በማዘጋጀት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ጋራንቲ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚከፈተው የጨረታ ማስታወቂያው 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀንን ጨምሮ አየር ላይ ከዋለ በኃላ በ11ኛው ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ 8፡30 ይከፈታል ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል። በተጨማሪም የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት በጨረታ ሰነድ የሚገለፅ ይሆናል።
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡-
- 011-6- 73 43 16/011-6-73-21-06 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።
- በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
- አድራሻ፡- ሲኤምሲ ሚካኤል ፊት ለፊት ድልድዩ አጠገብ ዴሉክስ ፈርኒቸር ጀርባ ያለው ህንጻ 4ኛ ፎቅ ግዥና ፋይናንስ ቢሮ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
cttx Advertising and Promotion cttx, cttx Art cttx, cttx Audio Visual, cttx Catering and Cafeteria Services cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Electrical, cttx Energy, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Equipment cttx, cttx Food and Beverage cttx, cttx Food Items and Drinks cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx Generators cttx, cttx Hand Tools and Workshop Equipment cttx, cttx Home Appliance and Supplies cttx, cttx House Furniture cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Machinery cttx, cttx Maintenance and Repair cttx, cttx Mechanical cttx, cttx Office Furniture cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Machines and Computers cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Others cttx, cttx Personal Care Products and Services cttx, cttx Printed Advertising Materials cttx, cttx Printing and Publishing cttx, cttx Promotional Items cttx, cttx Safety and Security cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Stationery cttx, cttx Textile, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx, Photography and Filming Service and Equipment cttx, Power and Electricity cttx