Your cart is currently empty!
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የሸንኮራ አገዳ ገለባ (ባጋስ) ከወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ወደ መተሃራ ስኳር ፋብሪካ ለማጓጓዝ የፓወር ትራክ መኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 25, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የጨረታ ማስታወቂያ
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተገለፀውን የሸንኮራ አገዳ ገለባ (ባጋስ) ከወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ወደ መተሃራ ስኳር ፋብሪካ ለማጓጓዝ የፓወር ትራክ መኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥ ይፈልጋል።
ጥቅስ አንድ – የሸንኮራ አገዳ ገለባ (ባጋስ) ከወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ወደ መተሃራ ስኳር ፋብሪካ ለማጓጓዝ የፓወር ትራክ መኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥ (Rent of power Truck)
በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
- ሕጋዊ የንገድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን የሀገር ውስጥ ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች ለአንድ ጥቅል የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሠዓት ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ህንፃ ግዥ ቡድን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 215 የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ገዝተው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሲገዙ የንግድ ፈቃድ ይዘው መቅረብ ይኖርባችኋል።
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሠነድ ጋር የታደሰ የንግድ ፈቃድ የአቅራቢዎች የምዝገባ ሠርተፍኬት እና ለጨረታ ማስከበሪያ 100.000.00 (አንድ መቶ ሺህ) የሚሆን በሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ (Proforma invoice) ላይ በማዘጋጀት በስም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እ.ኢ.አ. ህዳር 02 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጧቱ 4፡00 ሠዓት ድረስ ሜክሲኮ ፊሊፕስ ሕንጻ ቢሮ ቁጥር 119 ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በዕለቱ ህዳር 02 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧቱ 4:30 ሰዓት ላይ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 119 ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ፋብሪካው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 011 550 5607,011 550 5633
ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ሕንፃ
አዲስ አበባ
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ