Your cart is currently empty!
የሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በሮድ ፈንድ በጀት የሚ/አ/ከ/ዋና ማዘጋጃ ቤት በባለቤትነት ለሚያሠራው ዲች ጥገና እና ኮብልስቶን ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 25, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በሮድ ፈንድ በጀት የሚ/አ/ከ/ዋና ማዘጋጃ ቤት በባለቤትነት ለሚያሠራው
- ሎት 3 ዲች ጥገና በቁጥር 4 አጠቃላይ 0.66 ኪ/ሚ ፣
- ሎት 4 ኮብልስቶን ጥገና በቁጥር 2 0.245 ኪ/ሜ ፣
በግንባታ ሥራ የተደራጁ ማህበራቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላል።
1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
3. በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
5. ግብር ስለመክፈላቸው ከገቢዎች መ/ቤት ክሊራንስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
6. የጨረታ ሰነድ ከግዥ ኬዝ ቲም የሥራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን ብር 500/ አምስት መቶ ብር/ ከፍለው በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ።
7. ከአደራጅ መ/ቤት 5 የማህበር አባላት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
8. የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ሲመልሱ ቴክኒካሉን 1 ኦሪጅናልና 2 ኮፒ ፋይናንሺያሉን 1 ኦሪጅናልና 2 ኮፒ በሁለት ፖስታ በማድረግ እና በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9 የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት ሶስት 25,000/ሃያ አምስት ሺህ ብር/ ለሎት አራት 12,000/አስራ ሁለት ሺህ ብር/ ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የተረጋገጠ ቼክ በሁኔታ ላይ “ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፣ በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት እና በሁኔታ ላይ የተመሰረተ የመድህን ዋሰትና ለሚ አ/ከ/ አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በማለት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
10. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ 16ኛው ቀን ከቀኑ በ3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን በ4፡00 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
11. በጨረታው ማስታወቂያ ላይ የትርጉም ስህተት ቢኖር በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፀው ተቀባይነት ይኖረዋል።
12. ሰነዱን ሞልተው ወደ ጨረታ ሳጥን ለማስገባት ሲመጡ ተመዝግበውና ፈርመው ማስገባት አለባቸው።
13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት