የደ/ምዕ/ኢት/ህ/ክ/ መንግስት የሸካ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት የኤሌክትሮኒክስ፣ የፈርኒቸር እና ሞተር ሳይክል ግዥዎችን መፈጸም ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 25, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

የደ/ምዕ/ኢት/ህ/ክ/ መንግስት የሸካ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት

  • የኤሌክትሮኒክስ፣
  • የፈርኒቸርና ሞተር ሳይክል ግዥዎችን ለመፈጸም

ከዚህ በታች ያሉ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶችን ለጨረታ ይጋብዛል።

በዚሁ መሠረት፡- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በዘርፉ ፈቃዳቸውን ያሳደሱና በአገልግሎት አቅራቢ ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ ድርጅቶችን ይጋብዛል።

  1. የተዘረዘሩ መስፈርቶች ካሟሉት መካከል ጥረቱን የጠበቀ እና ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበውን በመምረጥ አሸናፊ ይለያል።
  2. ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ሆኖ በቀጣዩ የሥራ ቀን ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሠነዱ በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ በ4፡30 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት መሆኑን እናስታውቃለን።
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከሸካ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት የግዥ ፋ/ን/አስ/ር ቢሮ ቁጥር 9 በአካል/ በወኪሎቻቸው አማካይነት ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከማንኛውም በባንክ የተረጋገጠ CPO /በጥሬ ብር ለእያንዳንዱ 5,000 /አምስት ሺህ/ ብር ሆኖ ማስያዝ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች ዋጋ የተሞላበት ሰነድ አንድ ኦሪጅናል እና አንድ ኮፒውን በመለየት በማሸግ እንዲሁም የድርጀቱን ማህተም በማሳረፍ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  6. አሸናፊ ድርጅት መ/ቤቱ በሚፈልገውን የጥራት ደረጃ የጠበቀና በእስፔስፊኬሽን መሠረት ካላቀረበ በመንግስት ህግና ደንብ መሰረት መ/ቤቱ በህግ እንዲጠየቅ ይደረጋል።
  7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
  8. ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን፡-09-17-02-7673 እና 09-45-65 08-96 ላይ ይደውሉ።

የደ/ምዕ/ኢት/ህ/ክ/መንግስት የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት