Your cart is currently empty!
ሕብረት ባንክ አ.ማ. ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል
Reporter(Oct 26, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የሐራጅ ማስታወቂያ
ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፎቹ በኩል ለሰጠዉ ብድር በመያዣነት የያዛቸዉንና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ተሽከርካሪዎች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ሐራጅ(ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል።
| ተራ.ቁ. | የተበዳሪ ስም | የአስያዥ ስም | አበዳሪው ቅርንጫፍ | የሰሌዳ ቁጥር | የተሽከርካሪ አይነት | የስሪት ዘመን | የሻንሲ ቁጥር | የሞተር ቁጥር | የሐራጅ መነሻ ዋጋ ተ.ዕ.ታን ሳይጨምር) በብር | ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት | 
| 1 | ኤልሻይን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ/ | ኤልሻይን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ/ | መሐል አራዳ 
 | አአ-03- A53273 
 | አነስተኛ የሕዝብ–ኮሪያ ሀዩንዳይ | 2014 ኤ.አ.አ. 
 | KMHWG8 1R7EU621989 
 | G4KG-DA387443 | 1,530,000.00 | ኅዳር 04 ቀን 2018 ዓም ከጠዋቱ ከ4፡00 እስከ 5፡00 ሰዓት | 
| 2 | አቶ ፀጋ አዱኛ መስፍን | ወይ/ በረከት ዘሪሁን ምንዳዬ | ሀዋሳ 
 | አአ-02-C19382 | አውቶሞቢል ህንድ–ሱዙኪ | 2021 እ.አ.አ. 
 | MBHZF 6C1XNG176625 | K12MP-4297784 
 | 1,625,625.00 
 | ኅዳር 04 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5:00 እስከ 6፡00 ሰዓት | 
የሐራጅ ደንቦች፡–
- ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ.(Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ::ከባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ) ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም።
- ተሽከርካሪዎቹን ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከባንኩ የሕግ አገልግሎቶች መምሪያ ወይም ከቅርንጫፉ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ዕለት ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላል።
- የተሽከርካሪዎቹ ሐራጅ የሚካሄደው የሕብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ (ሕብር ታወር) 26ኛ ፎቅ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነው።
- በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ተበዳሪ እና አስያዥ ናቸው።
- ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል::ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት።
- የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል።
- ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል::ከፍተኛ ዋጋ ለሰጠ ተጫራች ደግሞ ያቀረበውን ዋጋ ባንኩ ሲቀበለው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ እንዲከፍል የሚገልፅ ደብዳቤ የሚሰጠው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው
- ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል::በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል:
- የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች የጨረታ አሸናፊ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ይከፍላል
- ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ የሕግ አገልግሎቶች መምሪያ በስልክ ቁጥር 0114 70 03 15 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።