Your cart is currently empty!
በቤ/ጉ/ክ/መንግስት የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ል/መምሪያ በከተማ አስተዳደሩ ስር ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በመደበኛና በመዘጋጃ ቤታዊ በጀት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 26, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-001/2018
በቤ/ጉ/ክ/መንግስት የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ል/መምሪያ በከተማ አስተዳደሩ ስር ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በመደበኛና በመዘጋጃ ቤታዊ በጀት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 – የደንብ ልብስ፣
- ሎት 2 – የስፖርት ትጥቅ፣
- ሎት 3 – ኤሌክትሮኒክስ፣
- ሎት 4 – የተለያዩ መኪናዎች፣
- ሎት 5 – የመንገድ ዳር የመብራት ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት በጨረታው ላይ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
1ኛ. ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የስራ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2ኛ. የተጨማሪ የእሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
3ኛ. ተጫራቾች የአቅራቢነት የምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4ኛ. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት(ቲን ነምበር)፤
5ኛ. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ አንኮንዲሽናል /CPO/ በእያንዳንዱ ሎት ለደንብ ልብስ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ለስፖርት ትጥቅና የመንገድ ዳር የመብራት ዕቃዎች ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ ማስያዝና በተጨማሪም ለተሽከርካሪ ግዥ ላይ ለምትወዳደሩት ብር 500,000 / አምስት መቶ ሺህ ብር/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የማንኛውንም የባንክ ቢድ ቦንድ የማንቀበል መሆኑን ጭምር እናሳውቃለን፡፡
6ኛ. ተጫራቾች የእቃውን ሙሉ ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዲስ አበባ መቤታችን በሚያመቻቸው ቦታ ላይ በአካል በመቅረብ ለተሽከርካሪ ግዥ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ እና ለሌሎች ለእያንዳንዱ ሎት 300 /ሶስት መቶ ብር/ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
7ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋቸውን ሞልተው በየሎቱ አንድ ቴክኒካል ኦሪጅናል እና ሁለት የቴክኒካል ኮፒ እና አንድ ፋይናንሻል ኦሪጅናልና ሁለት ፋይናንሻል ኮፒ ለእያንዳንዳቸው በተለያየ ፖስታ በማድረግ ፖስታውን በማሸግ ሰነዱን በገዙበት ክፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
8ኛ. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ እለት በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
9ኛ. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
10ኛ. አሸናፊው ድርጅት የሚለየው በነጠላ ዋጋ ሆኖ የተሻለ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበና በስፔካቸው መሰረት የቀረቡ መሆናቸው ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡
11ኛ. መምሪያው የተሻለ ዘዴና አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12ኛ. ተወዳዳሪ ድርጅቶች ከመኪናዎች እና ከኤሌክትሮኒክስ ግዥ ውጭ ለሚወዳደሩበት ዕቃ ናሙና ማቅርቦ ማሳየት አለባቸው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09-19-77-87-60/ 09-17-18-15-78/ 09-17-42-63-95/ 09-09-44~9652 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በቤ/ጉ/ክ/መ/ የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ል/መምሪያ