Your cart is currently empty!
ኮከብ ዱቄትና ፓስታ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለፋብሪካችን ግብዓት የሚውል ከጂቡቲ አዲስ አበባ ኮከብ ዱቄትና ፓስታ ፋብሪካ ሳሪስ ድረስ እና ከጁቡቲ ሀዋሳ ዱቄት አክሲዮን ማህበር ድረስ ለማጓጓዝ ይፈልጋል
Reporter(Oct 26, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
ኮከብ ዱቄትና ፓስታ ፋብሪካ የስንዴ ማጓጓዝ አገልግሎት ጨረታ የጨረታ ቁጥር 01/18
ድርጅታችን ኮከብ ዱቄትና ፓስታ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለፋብሪካችን ግብዓት የሚውል ከጂቡቲ አዲስ አበባ ኮከብ ዱቄትና ፓስታ ፋብሪካ ሳሪስ ድረስ እና ከጁቡቲ ሀዋሳ ዱቄት አክሲዮን ማህበር ድረስ ለማጓጓዝ በትራንስፖርት ዘርፍ የአንድ ኩንታል ዋጋ በማቅረብ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
1.በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ፣የብቃት ማረጋገጫ እና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሠርተፊኬት ያላቸው መሆኑ ይገባቸዋል
2. ተጫራቾች ለጠቅላላ የስንዴ ማጓጓዝ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ ብቻ ለብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው
3. የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውንና ከላይ የተጠቀሱትን ህጋዊ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ በማድረግ እና በአንድ ፖስታ በማሸግ እስከ ጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው
4. ጨረታው በዚያው ቀን ጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል
5. ተጫራቾች የንብረት ዋስትና መድን ሽፋን ያላቸውና inland (የመንገድ ላይ መድን ኢንሹራንስ) የገቡ መሆን ያለባቸውና የሞተር ኢንሹራንስ (የተሸከርካሪ) መድን ዋስትና ያላቸው መሆን አለባቸው
6. በመጨረሻም አሸናፊው ከተለየ በኃላ የሚጓጓዝ ውለታ በአስመጭውና በአጓጓዥ ድርጅት መካከል ውል የሚፈፀም ይሆናል
7. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 150 የማይመለስ በመክፈል ሰነዱን ከግዥ መምሪያ መውሰድ የሚቻል መሆኑን
8. አሸናፊ ድርጅት ውለታ ሲፈጽም የጠቅላላ የማጓጓዣ ዋጋውን 10% የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና በሲፕኦ ማቅረብ አለበት
9. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ሳሪስ 58 ማዞሪያ ኮከብ ዱቄትና ፓስታ ፋብሪካ
ስልክ ቁጥር፡- 09-11-16-12-67/09-11-26-60-18/011-419-15-25