የቃሊቲ አዲስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2018 ዓ.ም ለፅ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 26, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የጨረታ ማስታወቂያ

የቃሊቲ አዲስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2018 ዓ.ም ለፅ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን ማለትም፣

  • ሎት 1 አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች፣
  • ሎት 2 ቋሚ እቃ
  • ሎት 3 የደንብ ልብስ
  • ሎት 4 የጽዳት እቃዎች
  • ሎት 5 የመኪና ጎማ እና ጌጣጌጦች
  • ሉት 6 የህትመት ሥራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ

  1. ተጫራቾች በመስኩ የተሰማሩ፣ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የኢፌዴሪ የገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የተ.እ.ታ ተመዝጋቢዎች ለመሆናቸው ኮፒ ማስረጃ እና Tin No ሰርተፍኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ መሰረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያ /Financial/ ሰነድ ፣እንዲሁም አስፈላጊ ቴክኒካል ሰነዶችን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በመለየት ኦርጂናልና ኮፒውን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ፋይናንስ ክፍል በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 5,000 (አምስት ሺህ) ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/CPO/ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን መ/ቤቱ በሰጣቸው ሰነድ ላይ መሙላት እና በእያንዳንዱ የመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ ፊርማ በመፈረም የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
  6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና እንዲቀርብ ለተጠየቀባቸው ዕቃዎች ጨረታ ከመክፈቻ ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 5፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
  8. ተጫራቾች ውሉን ሲዋዋሉ ያሸነፉበትን የጠቅላላ ዋጋውን 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  9. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09042159873/0913149064 ደውሎ መጠየቅ ወይም ቃሊቲ ማሰልጠኛ ግቢ የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ቃሊቲ አዲስ ቅ/ጽ/ቤታችን ፋይናንስ ክፍል በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይቻላል።

የአ.አ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የቃሊቲ አዲስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት