Your cart is currently empty!
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ በክልሉ ውስጥ ለሚሰራው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራ አገልግሎት የሚውል ስሚንቶ ከለሚ ናሽንል ስሚንቶ ፋብሪካ በክልሉ ውስጥ ባሉ ከተሞች ማለትም ባህር ዳር፣ ደ/ማርቆስ፣ አዘዞ፣ ደ/ታቦር፣ ወልዲያ፣ ደሴ እና ደ/ብርሃን ከተሞች ለማጓጓዝ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የማጓጓዝ አገልግሎት ግዥዉን መፈጸም ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 26, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-09/2018 ዓ.ም
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ በክልሉ ውስጥ ለሚሰራው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራ አገልግሎት የሚውል ስሚንቶ ከለሚ ናሽንል ስሚንቶ ፋብሪካ በክልሉ ውስጥ ባሉ ከተሞች ማለትም ባህር ዳር፣ ደ/ማርቆስ፣ አዘዞ፣ ደ/ታቦር፣ ወልዲያ፣ ደሴ እና ደ/ብርሃን ከተሞች ለማጓጓዝ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የማጓጓዝ አገልግሎት ግዥዉን መፈጸም ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፤
3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. ተጫራቶች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ/ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጀዎች ፎቶ ኮፒ ከመጨረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በኮንስትራክሽን ኤጀንሲው አካውንት ቁጥር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013197966 በመክፈል የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ በመያዝ ከገንዘብ ያዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ17/02/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ቀን 02/03/2018 ዓ.ም ማግኘት ይቻላል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሲሚንቶ ማጓጓዝ ስራውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ስም በተከፈተ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000012858586 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ ኦሪጅናል ከፋይናንሻል ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ አድርገው ማስያዝ አለባቸው፡፡ ሆኖም የጠቅላላ ዋጋው 1% ከብር 500,000.00 /ከአምስት መቶ ሺህ ብር/ የሚበልጥ ከሆነ 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ ብቻ ማስገባት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማለትም ዋና እና ኮፒ (Original and Copy) በማለት በተለያየ ፖስታ በአንድ ኤንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሸግ በኤጀንሲው ግዥ ኢፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት /በአየር ላይ ከዋለበት/ ቀን ከ17/02/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ቀን 02/03/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
8. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ቫትንና ሌሎች ወጪዎችን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጀንሲው ዋና መ/ቤት ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ በቀን 02/03/2018 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 8፡30 ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ይከፈታል፡፡
10. የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
11. ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058-2-22-11–00 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058-3-22-05-155/ 058-2-22-11-07 በመደወል ወይም በኤጀንሲዉ ድረ–ገጽ www.arrca.gov.et ማግኘት ይችላሉ፡፡
13. ተጫራቾች በእያንዳንዱ የዋጋ መሙያ ገፅ ላይ ፊርማና መህተም ማድረግ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም በዋጋ መሙያው ላይ ስርስ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
ፖ.ሣ.ቁ.382
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ