የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለ150 ሰው የሚሆን ኬተሪንግ ከነአልሙናይ ድንኳን አገልግሎት የሚሰጥ እንዲሁም ከውጭ ለተጋበዙ 12 እንግዶች የመኝታና የምግብ አገልግሎት የሚሰጥ ከባለ 4 ኮከብ ሆቴል በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል


Reporter(Oct 26, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ህዳር 07/2018 . በጃንሜዳ ለሚያካሂደው 43ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር ላይ ለሚመጡ እንግዶች 150 ሰው የሚሆን ኬተሪንግ ከነአልሙናይ ድንኳን አገልግሎት የሚሰጥ እንዲሁም ከውጭ ለተጋበዙ 12 እንግዶች የመኝታና የምግብ አገልግሎት የሚሰጥ ከባለ 4 ኮከብ ሆቴል በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፡

  1. በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ በፌዴሬሽኑ የወጣውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የኮከብ ደረጃ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣የቲን እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 8 የሥራ ቀናት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በስምንተኛው ቀን 400 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት 430 ሰዓት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 (መሰብሰቢያ አዳራሽ) ይከፈታል።
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን አገልግሎት ቫትና ሰርቪስ ቻርጅን ጨምሮ ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
  6. ተጫራቾች ለሁለቱም መጠይቆች ማለትም ለኬተሪንግና ለእንግዶች የመኝታና የምግብ ዋጋ ለየብቻ መቅረብ አለባቸው።
  7. ፌዴሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንፃ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6

ለበለጠ መረጃ፡– 0116-47-97-94/ 0116-47-95-78 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

ፋክስ 0116-45-08-79

.. 13336

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *