Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 26, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 004/2018
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡– ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት
- በመንግሥት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገበ
- የንግድ ምዝገባ
- የቫት ሰርተፊኬት
ሎት1. የቪአይፒ ወንበሮች እና ጠረጴዛዎች
ሎት2. መጋረጃዎች (የዲኮር ጨርቅ)፣ ምንጣፍ እና የሣር ምንጣፍ
1. ከላይ በዝርዝር በቀረበው መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 100 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚችሉ ሲሆን፤ ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ከአደራጃቸው አካል የሚሰጥ የድጋፍ ደብዳቤ የጨረታ ሰነዱን በነጻ እንዲወስዱ ያስችላቸዋል፡፡
2. የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት1. 50,000.00(ሀምሳ ሺህ ብር)፣ ለሎት2 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በሲ.ፒ.ኦ፣ ቢድቦንድ ወይም ለጥቃቅንና አነስተኛ ከአደራጃቸው አካል የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ በማያያዝ ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት አንደኛ ፎቅ በሚገኘው አቅርቦት መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቴክኒካል ዶክመንት ዋና እና ቅጂ እንዲሁም የሚወዳደሩበትን ዋጋ ዋና እና ቅጂ በሚል በጉልህ በሚታይ መልኩ በመጻፍና የሚወዳደሩበትን ሎት በፖስታዎቹ ላይ በመግለጽ በአራት የተለያየ ፖስታ በማሸግ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያ ቴክኒክ ዋና ሰነድ ፖስታ ውስጥ ተያይዞ መገኘት አለበት፡፡
3. ስርዝ ድልዝ ያለውና ያልተፈረመ እንዲሁም በጉልህ የማይታይ አጠራጣሪ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
4. ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ 1ኛ ፎቅ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን፤ የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉለውም የጨረታ መክፈቻው ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
5. ድርጅታችን አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት