Your cart is currently empty!
ፀደይ ባንክ አ.ማ. ንብረቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Oct 26, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
ቁጥር ፀደይ ባንክ ደብ/ዲ/001/2018
ፀደይ ባንክ አ.ማ. በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የቀረቡትን ንብረቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪ ስም |
የንብረቱ አስያዥ ስም |
አበዳሪው ቅርንጫፍ |
ለጨረታ የቀረበው ንብረት መግለጫ |
የጨረታው መነሻ ዋጋ(በብር) |
ጨረታው የሚከናወንበት |
ጨረታው የወጣው |
|||||
|
ለጨረታ የቀረበው ንብረት |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የካርታ ቁጥር |
የቦታ ስፋት በካ/ሜትር |
ቦታ |
ቀን |
ሰዓት |
||||||
|
1 |
ወ/ሮ አስቴር በቀለ |
አቶ አወቀ ወርቁ |
ሚዳ ቅርንጫፍ |
ለመኖሪያ ቤት |
መራኛ ከተማ |
1179/2011 |
250 |
1,131,591.14 |
ፀደይ ባንክ ደ/ብርሃን ዲስትሪክት የስብሰባ አዳራሽ |
ህዳር 20/2018 ዓ.ም |
ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 5፡00 |
የመጀመሪያ |
|
2 |
ሀበሻ ኢንጅነሪንግና አርክቴክቸራል ኃ/የተ/የግል ማህበር |
አቶ ግሩም መኮንን |
ጠባሴ ቅርንጫፍ |
ለኢንዲስትሪ/ ኮርጌትድ ቦርድ/ አገልግሎት |
ደ/ብርሃን ከተማ ቀበሌ 08 |
ደብኢፖ/03/ 0047/2013 |
7,000 |
17,161,534.61 |
ፀደይ ባንክ ደ/ብርሃን ዲስትሪክት የስብሰባ አዳራሽ |
ህዳር 20/2018 ዓ.ም |
ከረፋዱ 5፡00 እስከ 7፡00 |
የመጀመሪያ |
የሀራጁ ደንቦች
1. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ ወይም ሃያ አምስት በመቶ (25%) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (ሲ.ፒ.ኦ) በፀደይ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
2. ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልፅ ደብዳቤ በፅሁፍ ሲደርሰው ብቻ ነው።
3. የጨረታ አሸናፊው አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል:: ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ በ ሶፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ያስያዘው ለባንኩ ገቢ ይሆናል:: በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሀራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል:: ላላሸነፉት ተጫራጮች ግን ያስያዙት ሲፒኦ በእለቱ ይመለስላቸዋል።
4. የሀራጁ አሸናፊ ወይም ገዢ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን የሊዝ ክፍያን ጨምሮ፤ ግብር፤ በዋጋው ላይ የሚታሰብ ተጨማሪ እሴት ታክስ ካለ ከስም ማዛወሪያ ጋር የተገናኙና ሌሎች ገዢ እንዲከፍለቸው በህግ የተወሰኑ ታክስና ግብሮች ገዢው/አሸናፊው/ ይከፍላል።
5. ተጫራቾች በሃራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ(የቀበሌ፣ ፓስፖርት ወይም ብሄራዊ መታወቂያ) መያዝ ይኖርባቸዋል::ተጫራቾች የህግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ህጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀትና ሃራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ግለሰብ ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ (የመተዳደሪያ ደንብ)፣ ቃለጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት።
6. ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል።
7. ለሃራጅ የቀረበውን ንብረትለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውምተጫራች ከአበዳሪ ቅርንጫፉ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጎብኘት ይችላል።
8. ጨራታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎቻቸው በተገኙበት ይካሄዳል:: ነገር ግን ተበዳሪውም ሆነ መያዣ ሰጪው ባይገኙም ጨረታው በሌሉበት ይካሄዳል።
9. ንብረቱን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ /ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም:: ገዢው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያዘ ለሚኖር ወጪ ገዢው ሃላፊነቱን ይወስዳል።
10. በወንድ አንቀፅ የተጠቀሰው ለሴት እና ህጋዊ ሰውነት ላላቸው ድርጅትም ያገለግላል።
11. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. ለበለጠ ማብራሪያ ፀደይ ባንክ አ.ማ 0116 812 313 በስራ ሰዓት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ፀደይ ባንክ አ.ማ