Your cart is currently empty!
ሞ-ያ ምግብ ድርጅት በሸዋዙሪያ፤ ደሴ፣ አላማጣ፣ ወልዲያ፤ ደብረ ማርቆስ፣ ፍኖተ ሰላም፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፤ ጅማ፣ ነቀምት፣ በደሌ፣ ዲላ፣ ሃገረሰላም፣ አዋሽ፣ አሰበ ተፈሪ፣ ድሬዳዋ፣ ሀረር፣ ጅግጅጋ፣ ሆሳዕና፣ ወላይታ ሶዶ እና አርባ ምንጭ ..ወዘተ ባሉ የሽያጭ ቦታዎች የብስኩት ምርቶቹን የሚያከፋፍሉለት አከፋፋዮች ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 28, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የሞ–ያ ምግብ ድርጅት ወኪል አከፋፋዮች መሆን ለሚፈልጉ
የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ
ሞ–ያ ምግብ ድርጅት ተወዳጅ የሆነውን ሞ–ያ ብስኩት በተለያየ ፍሌቨር እና ጣዕም በጥራት የሚያመርት ኩባንያ ሲሆን ፡–
በሸዋዙሪያ፤ደሴ፣ አላማጣ፣ወልዲያ፤ ደብረ ማርቆስ፣ ፍኖተ ሰላም፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፤ጅማ፣ ነቀምት፣ በደሌ፣ ዲላ፣ ሃገረሰላም፣ አዋሽ፣ አሰበ ተፈሪ፣ ድሬዳዋ፣ ሀረር፣ ጅግጅጋ፣ ሆሳዕና፣ ወላይታ ሶዶ እና አርባ ምንጭ ..ወዘተ ባሉ የሽያጭ ቦታዎች የብስኩት ምርቶቹን የሚያከፋፍሉለት አከፋፋዮች ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት፤
ብቁ አከፋፋዮች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን ይገባቸዋል።
1. ለዚሁ ንግድ የሚሆን አስፈላጊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
2. ለዚሁ ሥራ የሚሆን ፤
- ደረጃውን የጠበቀ መጋዘን፤
- ለማከፋፈያ የሚሆኑ መኪኖች፤
- በቂ የካፒታል መጠን ያለው፤
- በየቀኑ ስራውን በአግባቡ እና በትጋት መሥራት የሚችል፤
- የፋብሪካ ምግብ ውጤቶች ማከፋፈል ልምድ ያለው፤
- በተሰጠው የማከፋፈያ ክልል ውስጥ የድርጅቱን ምርቶች ለሁሉም ደንበኞች ማከፋፈል የሚችል፤ … ወዘተ ሲሆን ተጫራቾች ለዚህ የተዘጋጀውን ቢጋር /Terms of Reference / ሀይሌ ጋርመንት አካባቢ በሚገኘው የፋብሪካው ዋና መስሪያ ቤት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) መግዛት ይችላሉ፡፡
3. የኢትዮጵያ የግብር ሕግ የሚጠይቀውን መስፈርት አሟልተው መስራት የሚችሉ፤
4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት (አንድ ወር )ክፍት ይሆናል፤
5. ተጫራቾች ከላይ በተጠቀሰው አንድ ወር አስፈላጊ ሰነዶችን በፖስታ አሽገው በፋብሪካው ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይችላሉ፤
6. ጨረታው በ35ኛው ቀን (ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ) በተከታዩ ቀን ይከፈታል ፤ የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታው እንዳይከፈት አያደርገውም፤
7. ድርጅቱ ጨረታውን በተዘጋጀው መስፈርት መሠረት ገምግሞ ከተመረጡት ጋር አስፈላጊውን ውል ይፈራረማል፤
8. ድርጅቱ አከፋፋዮችን ለመምረጥ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡
ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አመልካቾች ኃይሌ ጋርመንት ንፋስ ስልክ ላፍቶ እንዱስትሪ መንደር በሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 30 ቀናት ማመልከት ይቻላል።
የስልክ አድራሻ፤ ሞ–ያ ምግብ ድርጅት
ስልክ ቁጥር ፤ 0116 292 969 ፣ 0990 392 838 ፤ 0961 522 838 (አዲስ አበባ)
የሞ–ያ ምግብ ድርጅት