Your cart is currently empty!
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚሆን ቋሚ እቃዎች ማለትም ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 27, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የመለያ ቁጥር GGWW/0003/2018
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚሆን ቋሚ እቃዎች ማለትም ኤሌክትሮንክስ እና ፈርኒቸር ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ለግዥ የቀረቡ እቃዎችና የጨረታ ማስከበሪያ CPO
- ሎት አንድ ፡ ለኤሌክትሮኒክስ ፡ የጨረታ ማስከበሪያ 30,000 ብር
- ሎት ሁለት ፡ ለፈርኒቸር የጨረታ ማስከበሪያ 20,000 ብር
ስለሆም ተወዳዳሪዎች ፡–
1. የዘመኑ ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ የቫትና የቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. የአቅራቢነት የምስከር ወረቀት በኦላይን /online ሲስተም የተመዘገበ መሆን አለበት።
3. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት ጨረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆነ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መምጣት አለባቸው።
4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስከ 21ኛው ተከታታይ የስራ ቀናት 8፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 100 ብር/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመቅረብ የጨረታው ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ዶከመንት ሲያቀርቡ፣ ሀ/ ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት እና ለ/ ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒውን ኮፒ በማድረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በሰም በማሸግ ከላይ የተጠቀሱት የጨረታ ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በሰም ሁሉንም በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ ፋይናንሻል ዶክመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ሀያ አንድ ተከታታይ የስራ ቀናት ከገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. የጨረታው ማስከበሪያ ሲፒኦ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም መሰራት አለበት።
7. የጨረታው ሰነድ በ21ኛው ተከታታይ የስራ ቀናት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይታሸጋል። ከቀኑ 8፡30 ደግሞ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
8. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ ፡–
- በግዢ ኤጀንሲ በዕቃ አቅርቦት ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶችም መወዳደር አይችሉም
- የቫት 7.5 ለወረዳው ገቢ የሚቆርጥ
- ተጫራቾች ተጫርተው ያሸነፉዋቸው እቃዎች የጥራት ችግር ያለባቸው መሆናቸው በቴክኒክ ጥሪት ኮሚቴ ከተረጋገጠ ተመላሽ መሆኑን፤
- ተጫራቾች ተጫርተው ያሸነፉዋቸው ማንኛውም እቃ የወረዳው ማዕከል ማለትም ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መሀል አምባ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የወረዳው ማእከል ርቀት ከአዲስ አበባ 116 ኪሜ ነው።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።
ለበለጠ መረጃ 011 336 0631 / 011 336 0146
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት