Your cart is currently empty!
በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በሰቃ አፀደ ህፃናትና የመ/ደ/ት/ቤት ለ2018 በጀት አመት የደንብ ልብስ፣ አላቂ የት/እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የስፖርት ትጥቅ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች እና ሌሎች አላቂ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 28, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
አንደኛ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በሰቃ አፀደ ህፃናትና የመ/ደ/ት/ቤት ለ2018 በጀት አመት የደንብ ልብስ፣ አላቂ የት/እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የስፖርት ትጥቅ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች እና ሌሎች አላቂ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች ሊያሟሉ የሚገባቸውን
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤
3. ቲን/ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፤
4. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር ከታች በተዘረዘረው መሰረት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በሰቃ አፀደ ህፃናትና የመ/ደ/ት/ቤት የፋ/ግ/ን/አስ/ደ/የስ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ ኦሪጅናል እና ኮፒ ብሎ በመፃፍ በተለያየ ካኪ ፖስታ ፊርማና ማህተም በማስፈር ማቅረብ፤ የጨረታ ሰነዱ የመጨረሻ ማስረከቢያ ቀን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛ ቀን 4፡00 ሰዓት ደረስ ከቆየ በኃላ የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ከተማ አስ/አቃ/ቃ/ክ/ከ/የበሰቃ አፀ/ህ/ትና የመ/ደ/ት/ቤት ይከፈታል፡፡
8. የጨረታ አሸናፊዎችም ተለይቶ በተገለፀው ተከታታይ 7 የስራ ቀናት ውስጥ አሸናፊዎች የውል ማስከበሪያ 10/100 በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው፡፡ ተሸናፊዎች ደግሞ ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ መውሰድ ይችላሉ፡፡
9. አሸናፊዎች በገቡት ውል መሰረት እቃዎችን በሰቃ አፀደ ህፃናት የመ/ደ/ት/ቤት የፋ/ግ/ን/አስ/ደ/የስ ሂደት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
10. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
11. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ አንድ ቀን በፊት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
12. ለሀገር ውስጥ እቃዎች ቅድሚያ ይሰጣል፡፡
13. ለናሙና የሚያቀርቡት ዕቃዎች ላይ ምልክት ማድረግ ከውድድር ውጪ ያደርጋል፡፡
14. ለናሙና ከ1 ሜትር በላይ /በጣቃ አንቀበልም፡፡
15. ጥቃቅንና አነስተኛ ደብዳቤ ይዘው ለሚመጡ ተጫራቾች ሀገር ውስጥ ምርት ላይ ብቻ መሳተፋቸውን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
|
ተ.ቁ |
መግለጫ |
የእቃው አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ በብር |
|
1 |
ሎት 1 |
የደንብ ልብስ |
38,000 |
|
2 |
ሎት 2 |
አላቂ የት/እቃዎች |
9,000 |
|
3 |
ሎት 3 |
ቋሚ እቃ |
13,000 |
|
4 |
ሎት 4 |
የፅዳት እቃዎች |
33,000 |
|
5 |
ሎት 5 |
ሌሎች አላቂ ዕቃዎች |
20,000 |
አድራሻ፡– አቃቂ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር :- 011-4-71-51-66/ 011-047-10-52-031
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት በሰቃ አፀደ ህፃናትና የመ/ደ/ት/ቤት