Your cart is currently empty!
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ልዩ ልዩ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 28, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት ለመምሪያውና በስሩ ለሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች ለስራ አገልግሎት የሚውል ልዩ ልዩ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑ ተጫራቾች ከስር በየሎቱ የተቀመጠውን የጨረታ ማስከበሪያ የብር መጠን በሲፒኦ በመ/ቤቱ ስም በማስያዝ መወዳደር ይችላሉ።
| ሎት 1 የፅህፈት ዕቃዎች | የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 6,000.00 | 
| ሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች | የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 4,000.00 | 
| ሎት 3 ኤሌክትሪክ እቃዎች | የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 5,000.00 | 
| ሎት 4 ግንባታ እቃዎች | የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 5,000.00 | 
| ሎት 5 ህንፃ መሣሪያ | የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 6,000.00 | 
| ሎት 6 ቋሚ እቃዎች | የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 6,000.00 | 
| ሎት 7 አልባሳት | የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 5,000.00 | 
| ሎት 8 የህትመት ውጤቶች | የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 6,000.00 | 
| ሎት 9 ህክምና መድሀኒት ሪኤጀንትና የህከምና እቃዎች | የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 5,000.00 | 
| ሎት 10 የኤሌክትሮኒክስ (የቢሮ መሣሪያዎች) ጥገና እና እድሣት | የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 4,000.00 | 
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፦
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እና በጨረታው ለመወዳደር ፍላጐት ያላቸው የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድረ ገጽ ላይ በአቅራቢነት ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል እና ከግብር ነፃ መሆኑን የሚያስረዳ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ለተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ 100 ብር በመክፈል የተዘጋጀዉን የጨረታ ሰነድ ልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 ከቀኑ 7፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ 5ተኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 11 የስራ ቀናት በልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ 5ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት ውጭ ዘግይቶ የደረሠ ተጫራች ተቀባይነት የለውም።
- ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት መምሪያው በሚያዘጋጀው ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጎልም፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን እሽጉ ይከፈታል።
- ተጫራቾች እንደ አስፈላጊነቱ ናሙና ሳምፕል የሚያስፈልጋቸውን እቃዎች የጨረታ ሳጥን ከመክፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎቶች ናሙና ማቅረብ አለባቸው እንዲሁም አንዳንድ ዕቃዎች ዝርዝር የዕቃ መለያ ፕሮፖዛል ወይም (እስፔስፊኬሽን) እና ሥሪቱ ሀገር መጥቀስ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ውጭና ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፋባቸዉን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡መስሪያ ቤቱ ተጫራቾች ከአሸነፉት እቃ ላይ 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በአቅርቦትና በአገልግሎት አሠጣጥ ብቃትና ጥራት እንዲሁም በወቅቱ ማቅረባቸውን ከአሁን በፊት የተመሠከረለት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ቢሆን ይመረጣል።
- በጉዞ ወቅት ወይም በርክክብ ወቅት የተበላሹና የተሰበሩ እንዲሁም የማይሰሩ እቃዎች ቢገኙ ወይም ተመሳስለው የተሰሩ እቃዎች ቢያስረክብ ተመላሽ የማድረግና በራሱ ወጪ የመተካት ግዴታ አለበት ለሠጠውም እቃዎች ዋስትና መስጠት ግዴታ አለበት።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት መድሃኒት የአገልግሎት ቆይታ ጊዜ ሁለት ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ሲያስገቡ ግዥ ክፍል ባዘገጀው ፎርም ላይ ዋጋቸውን ማስገባት አለባቸው፡፡ በራሳቸው ፎርም ዋጋቸውን ካስገቡ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡–
አድራሻ ልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጎማ ቁጠባ 5ተኛ ፎቅ ግዥ አስተዳደር ከፍል ስልክ ቁጥር 0115 -57-33 -14 ደውለው መረዳት ይችላሉ።
በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ