Your cart is currently empty!
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተለያዩ የተወረሱ ዕቃዎችን በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 28, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተገለጹ የተለያዩ የተወረሱ ዕቃዎችን በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ጨ.ቁ 04/2018 ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
ዘርፍ |
የጨረታው ዓይነት |
እቃው ያለበት ቦታ |
|
1 |
ጫማዎች |
ሐራጅ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
2 |
ኮስሞቲክስ ዕቃዎች |
ግልጽ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
3 |
ኤሌክትሮኒክስ |
ግልጽ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
4 |
የመኪና መስታወት ዕቃዎች |
ግልጽ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
በመሆኑም የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆነን እናሳውቃለን።
1. በጨረታው ሽያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ከግብር ስብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ (ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ክሊራንስ) ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የሚወዳደሩበት የጨረታ ዓይነት መነሻ መሸጫ ዋጋው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነ ማንኛውም እቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማስረጃ ማቅረብ አያስፈልገውም። በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ያለባቸው ሲሆን ለሐራጅ ጨረታ ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች በጨረታ መክፈቻው ቀንና ሰዓት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ1፡00-5፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በመገኘት ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 30 በመምጣት መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
3. ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና በሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው ጫማዎች ብር 150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ለጨረታ ዋስትና (CPO) በቅ/ጽ/ቤቱ ስም ETHIOPAN CUSTOMS COMMISSION SEMERA BRANCH OFFICE በሚል በባንክ አሰርተው ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰመራ እና ከሎጊያ ቅርንጫፎች ብቻ መዘጋጀት ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ።
|
ተ.ቁ |
የቅ/ጽ/ቤቱ ስም |
የጨረታው ዓይነት |
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ |
የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት |
ግልጽ ጨረታ |
እስከ 24/02/2018 ዓ.ም |
በ25/02/2018 ዓ.ም በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ3፡45 ሰዓት ይከፈታል። |
|
2 |
ሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት |
ሐራጅ ጨረታ |
እስከ 24/02/2018 ዓ.ም |
በ25/02/2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል። |
5. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል።
6. ተጫራቾች ያስያዙትን ዋስትና (CPO) በተመለከተ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የዕቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጽ በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
7. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለባቸው ሲሆን ይህን ባይፈጽሙ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን የእቃውን ዋጋ ገቢ አድርጎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል። ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጣ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል።
8.ቅ/ጽ/ቤቱ ለጨረታ የቀረበውን እታ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው።
9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 033-3-66-23-02/033-3-66-50-04 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት