በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በሸገር ከተማ የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለገላን ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የስፖርት ትጥቆች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 27, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በሸገር ከተማ የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለገላን ክ/ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የስፖርት ትጥቆች አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለጸውን መመሪያ መረጃዎች በማቅረብ/ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

1.በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፍሉ፡፡

2.በአቅራቢዎች ዝርዝር ተርታ የተመዘገቡ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡

3.የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin/ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡

4. የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

5.ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት ( 15) ተከታታይ የሥራ ቀናት እና በሥራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 2000.00 (ሁለት ሺህ) ብር በገላን ክ/ከተማ ገቢዎች ባለሥልጣን ጽ/ቤት በመክፈል ሰነዱን ከገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ ፡፡

6. ተጫራቾች የሚያቀርበበትን የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር (ሰነድ) ዋና እና ኮፒ ለያብቻ በታሽገ ኤንቨሎፕ በፖስታ/በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሉት አስራ አምስት ( 15) ተከታተይ የሥራ ቀናት ድረስ በገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት ባዘጋጀነው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል ።

7. ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ ተዘግቶ/ ልክ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገላን ክ/ከተማ 7 /ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ከልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና ብር 50,000(አምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ / CPO/ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

9. ተጫራቾች የጨረታውን አሸናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10 % በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል፡፡

10. ተጫራቾች የጨረታውን አሸናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ ውል ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡

11. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተገለፀው መስረት የተጫረተበትን ዕቃ ናሙና Sample/ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

12. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ለይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለው ማለት አይችልም፡፡

13. የመወዳደሪያ በጨረታ ሰነዱ በተዘረዘረው መሠረት ተሞልቶ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

15. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011 4 45 01 82 በመደወል እና በአካል ተገኝቶ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

አድራሻ፡- በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት/ገላን

በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *