የአፋር ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የሴቶች ደህንነት መጠበቂያ (Women Safe House) ስራ ለማስጀመር የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎችን እና ለአንድ መስኮት አገልግሎት (One Stop Center) የሚውሉ ማቴሪያሎች፣ የጉዳይ አያያዝ ስርአት ለማጠናከር የሚያግዙ እና ለቢሮው ስራ አገልግሎት የሚውሉ ማቴሪያሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 27, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ግዥ 001/2018

የአፋር ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በ UNICEF እና UNFPA የበጀት ድጋፍ በሚያከናውናቸው ተግባራት፦

1. በ UNFPA የበጀት ድጋፍ ጥቃት ለሚደርስባቸው ሴቶችና ህጻናት የተሟላ ምላሽ መስጠት የሚያስችል ስርአትን ለመዘርጋት እንዲቻል የሴቶች ደህንነት መጠበቂያ ( Women Safe House ) ስራ ለማስጀመር የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎችን እና

2. በ UNICEF የበጀት ድጋፍ ለአንድ መስኮት አገልግሎት ( One Stop Center) የሚውሉ ማቴሪያሎች፣ የጉዳይ አያያዝ ስርአት ለማጠናከር የሚያግዙ እና ለቢሮው ስራ አገልግሎት የሚውሉ ማቴሪያሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች በቅድሚያ።

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

4. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤

5. በመንግስት ግዥ ለመሳተፍ በአቅራቢነት የተመዘገቡ፤

6. በመንግስት መ/ቤቶች ጨረታ እንዳይሳተፉ ያልታገዱና በመንግስት ግዥ የግልጽ ጨረታ አፈጻጸም መመሪያ መሰረት ለመወዳደር ብቁ የሆኑ፤

7. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃ ዝርዝር መግለጫ ወይም አስፈለጊውን መረጃ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፍል ከአፋር ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 07 የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ። ከተጠቀሰው ቀን በኃላ ምንም አይነት የሰነድ ሽያጭ የማይካሄድ መሆኑን መታወቅ ይኖርበታል።

9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሠመራ ከተማ በአፋር ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ በተጠናቀቀ በ 2ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል።

10. የጨረታው መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ባለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡

11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% (አንድ ከመቶ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።

12. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በ1 /አንድ/ ኦሪጅናልና በ1 ኮፒ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለአፋር ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 07 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በጨረታው መዝጊያ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አፋር ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክተር ድረስ በአካል በመገኘት መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

14. አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈጽሙ ከውሉ ጠቅላላ ዋጋ 10% ለውል ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ CPO ማስያዝ ያለባቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል።

15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ አልያም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

16. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከአፋር ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የግዥ ፋ/ንብ/አስ/ዳይሬክተር ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር +251 92 000 0428 እና +251 91 155 0984 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

የአፋር ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ