የኮምቦልቻ ዶሮ ሀብት ልማት ኢንተርፕራይዝ ለ2017 በጀት ዓመት የሂሳብ ምርመራ ወይም ኦዲት ለማስደርግ እና የ2018 በጀት ዓመት ግዥ የዶሮ መኖ ጥሬ እቃዎች፣ የተመጣጠነ /የተዘጋጀ/ የዶሮ መኖ፣ የዶሮ ክትባት /መድኃኒት/፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ የቧንቧ እቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች እና የማዳበርያ ከረጢት፣ የሰራተኞች ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 27, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የኮምቦልቻ ዶሮ ሀብት ልማት ኢንተርፕራይዝ ለ2017 በጀት ዓመት የሂሳብ ምርመራ ወይም ኦዲት ለማስደርግ እና የ2018 በጀት ዓመት ግዥ የዶሮ መኖ ጥሬ እቃዎች፣ የተመጣጠነ /የተዘጋጀ/ የዶሮ መኖ፣ የዶሮ ክትባት /መድኃኒት/፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ የቧንቧ እቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች እና የማዳበርያ ከረጢት፣ የሰራተኞች ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ያላቸው፡፡

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡

3. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ሆኖ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የድርጅቱን ስም፣ አድራሻ፣ ማህተም፣ ፊርማ በማድረግ በሚነበብ መልኩ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ለኦዲትና ለመኖ ጥሬ አቃ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ ለሌሎቹ ገዥዎች ብር 300/ ሶስት መቶ ብር በመክፈል በሽያጭ ክፍል ቢሮ ማግኘት ይቻላል፡፡

5. የተመጣጠነ የተዘጋጀ የዶሮ መኖ አቅራቢ ተጫራቾች የብቃት እና የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት ኦርጅናሉን በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ሕጋዊ ማህተም በማድረግ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከ17/2/2018 ዓ.ም እስከ 27/2/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም በ27/2/2018 ዓ.ም 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የዋጋውን 1/አንድ/ ከመቶ በጥሬ ገንዘብም ሆነ በሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡

9. የእቃው ርክክብ በተመለከተ ኮምቦልቻ ዶሮ ሀብት ልማት ኢንተርፕራይዝ ግቢ ድረስ ማስረከብ የሚችሉ፡፡

10. ጨረታውን ተወዳድሮ ከሚያሸንፍ አቅራቢ እስከ 50 በመቶ ተጨማሪ ማዘዝም ሆነ ቀንሶ መግዛት ይቻላል፡፡

11. የጨረታ አሸናፊ አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የዋጋውን የውል ማስከበሪያ 10% ሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ አስይዞ ውል መግባት የሚችሉ፡፡

12. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 033 351 0660

የኮምቦልቻ ዶሮ ሀብት ልማት ኢንተርፕራይዝ