Your cart is currently empty!
ስፋቱ 162 ካ.ሜትር የሆነ ቤትና ቦታ የጨረታ ማስታወቂያ
Addis Zemen(Oct 29, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የጨረታ ማስታወቂያ
አፈ/ከሳሽ… ፀደይ ባንክ አማ እራስ ጋይንት ቅርንጫፍ
አፈ-ተከሳሽ .
1. ታርቄ ምስጋናው አባተ
2. ወ/ሮ ሠናይት እርቅይሁን መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ
በ1ኛ የአፈ/ተከሳሽ በታርቄ ምስጋናው ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በነፋስ መውጫ ከተማ ቀበሌ 03 በአዋሳኝ ምስራቅ ቢራራ አበባው ምዕራብ መንገድ ስሜን አዲሱ ሲሳይ ደቡብ ደሳለኝ አስፋው ስፋቱ 162 ካ.ሜትር የሆነ ቤትና ቦታ በመነሻ ዋጋው 1,093,953.08 / አንድ ሚሊዮን ዘጠና ሶስት ሺ ዘጠኝ መቶ ሀምሳ ሶስት ብር ከስምንት ሳንቲም/ በሆነ በጨረታ ለመሸጥ የጨረታ ማስታወቂያ በእናንተ በኩል በማስነገር ውጤቱ እንዲቀርብ የጨረታ ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ 30 ቀናት ሲሆን ከጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ኅዳር 13 ቀን 2018 ዓ.ም ይሆናል፡፡ የጨረታ አሸናፊው የሚለየው ኅዳር 13 ቀን 2018 ዓ.ም ቤቱ በሚገኝበት ቦታ መሆኑን እየገለጽን ውጤቱ ለፍ/ቤቱ የሚገለፀው ኅዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ይሆናል፡፡ አሸናፊው ያሸነፈበትን ገንዘብ 1/4 ኛውን ወዲያውኑ የማስያዝ ግዴታ አለበት፡፡ ፍ/ቤቱ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ጨረታው የሚካሄደው በ13/3/2018 ዓ.ም ከ4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ሲሆን በጨረታው ሰዓት ከነፋስ መውጫ ከተማ አስ/03 ቀበሌ የቀበሌው ምድብተኛ ፖሊስ የፍ/ቤቱ ሐራጅ ላይ በተገኙበት ያጫርታሉ የጨረታው ደብዳቤ በሚሽጠው ቤት ላይ በቀበሌው ማዕከል በነፋስ መውጫ ከተማ ከተማና መ/ል/ጽ/ቤት እና ለሕዝብ ግልፅ አመች በሆነው ቦታ ላይ እንዲለጠፍ ፍ/ቤቱ እያዘዘ ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ተገኝቶ መጫረት እንዳለበት ፍ/ቤቱ አዟል፡፡
በአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት በደ/ጎን/አስ/ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የፍታብሔር ዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ዋና የሥራ ሂደት