በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የቃሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ ቡድን ለቃሉ ወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የግንባታ እቃዎች፣ የውሃ እቃዎች፣ የመኪና እቃዎች እና አመታዊ የመኪና ጥገና ጋራዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 29, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የቃሉ ወረዳ ገንዘብ /ቤት የግ//አስ ቡድን ለቃሉ ወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት-1 – የጽህፈት መሳሪያ ሎት -2- የጽዳት እቃዎች፣ ሎት -3 ኤሌክትሮኒክስ፣ሎት -4-ፈርኒቸር ፣ሎት-5- የግንባታ እቃዎች ሎት 6 የውሃ እቃዎች ሎት-7- የመኪና እቃዎች ሎት 8 አመታዊ የመኪና ጥገና ጋራዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

1. የጨረታ መለያ ቁጥር////002/2018

2. ተጫራቾች ህጋዊ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ቲን ነምበር ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና መረጃ ኦርጂናል እና የማይመለስ ኮፒ እንድሁም ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መታሸግ ሲኖርበት የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

3. የሚፈለገውን የእቃ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የሚያቀርቡት ዋጋ ከነቫቱ ነው።

4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 18/02/2018 / ጀምሮ እስከ 2/03/2018 / 1130 ሰዓት ድረስ ቃሉ ወረዳ ገንዘብ /ቤት ቢሮ .9 በመምጣት የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በጥሬ ገንዘብ በመክፈል መግዛት ትችላላችሁ።

5. ተጫራቾች ለሎት -1- 20,000 /ሀያ ሺህ ብር/፤ለሎት-2- 3,000 /ሶስት ሺህ ብር/ ለሎት– 3- 10,000 /አስር ሺህ ብር/፤ለሎት -4- 10,000/አስር ሺህ ብር/፣ለሎት5- 40,000/ አርባ ሺህ ብር/፣ለሎት-6- 20,000/ሃያ ሺህ ብር/ለሎት-7- 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ለሎት8- 3,000 /ሶስት ሺህ ብር/ በሲ.. ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው፡፡ የሚያስይዙት የጨረታ ማሰከበሪያ በቢድ ቦንድ ከሆነ 60 ቀን ያነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ተቀባይነት የለውም።

6. የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከሎት1 እስከ 7 ላሉት ሎቶች የጠቅላላ ዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ እንድሁም ለሎት 8 3% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል።

7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ዋናና ኮፒ በማለት ለየብቻ በፖስታ አሽጎ ስምና አድራሻውን በመጻፍ ቃሉ ወረዳ ገንዘብ /ቤት //አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው  የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 03/03/2018 ከጠዋት 400 ሰዓት ድረስ ብቻ ፖስታውን ማስገባት የሚቻል ሲሆን በዚሁ እለት 400 ላይ ታሽጎ 430 ሰዓት ላይ ተጫራቾ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በመክፈቻው እለት የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም።

8. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የበኣል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰኣት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰኣት ይከፈታል።

9. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች በአሸነፈበት ዋጋ በፍትህ /ቤት ቀርቦ ውል ለመውሰድ ፍቃደኛ የሆነ መሆን አለበት፡፡

10. ሎት 8 የአንዱን ዋጋ በመሙላት አመታዊ የጥገና ኮንትራት ውል የሚወሰድ ሲሆን በውሉ መሰረት የሚፈለገውን ጥገና በአጭር ጊዜ ጠግኖ ለመጨረስ ፍቃደኛ መሆን ሲኖርበት ሎት 1፣ሎት-2- ሎት 3- ሎት 4፣ሎት-5 ሎት-6 እና ሎት-7 የተገለጹት እቃዎች በአንድ ጊዜ በጥቅል ንብረት ክፍል የሚገቡ መሆኑ መታወቅ አለበት።

11. ውድድሩ የሚካሄደው በእያንዳንዱ ሎት ድምር ነው።

12. ሁሉም የጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማ መኖር የሚገባው ሲሆን ስርዝ ድልዝ ሲያጋጥም በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል።

13. /ቤቱ ከአሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ከአሸነፈው እቃ ወይም ገንዘብ መጠን ላይ 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።

14. ተጫራቾች ክልሉ ላወጣቸው የግዥ አፈጻጸም መመሪያዎች ተገዥ መሆን ሲኖርባቸው ማሸነፉ ከተነገረ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራስን ማግለል አይቻልም፡፡

15. አሸናፊው ተወዳዳሪ ኦርጂናል እቃዎችን ማቅረቡ ግዴታ ሲሆን ተጫራቾች ሰነድ ሲገዙ /ቤታችን ያዘጋጃቸውን ናሙናዎች በማየት በናሙናው መሰረት ማቅረብ አለባቸው፡፡

16. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

17. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር ማስረጃ ከፈለጉ ቃሉ ወረዳ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 551 4657 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

በአብክመ /ወሎ ዞን የቃሉ ወረዳ ገንዘብ /ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን

ምቦልቻ