Your cart is currently empty!
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደ/ወሎ ዞን በወግዲ ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት በዋንዋሽ ፕሮግራም በአለም ባንክ በጀት በወግዲ ቁጥር አንድ ትምህርት ቤት ባለ አራት ቀዳዳ የወንዶችና የሴቶች መፀዳጃ ቤት 1 የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ (MHM)፣ ባለ12/ባለ አስራ ሁለት/ ጡት የዕጅ መታጠቢያ የውሃ ቧንቧ እና 1/ አንድ/ የቆሻሻ ማቃጠያ በሀገራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 29, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ሀገራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደ/ወሎ ዞን በወግዲ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በዋንዋሽ ፕሮግራም በአለም ባንክ በጀት በወግዲ ቁጥር አንድ ት/ቤት ባለ አራት ቀዳዳ የወንዶችና የሴቶች መፀዳጃ ቤት 1 የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ (MHM)፣ ባለ12/ባለ አስራ ሁለት ጡት የዕጅ መታጠቢያ የውሃ ቧንቧ እና 1/ አንድ የቆሻሻ ማቃጠያ በሀገራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ጽ/ቤታችን ይጋብዛል። በዚህም መሰረት ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- የዘመኑ የታደሰና ህጋዊ ፈቃድ ያለውና የንግድ ስራ ዘርፍ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ነምበር ያለው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- የግዥ መጠን ከ200,000/ሁለት መቶ ሽህ ብር በላይ ከሆነ ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ሻት ተመዝጋቢ መሆን ይገባቸዋል
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጨረታ ላይ የንግድ ሚኒስቴር ባወጣዉ የንግድ ስራ ፍቃድ ኮድ መሰረት ንግድ ፈቃዳቸዉን ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ሲመጡ ከላይ ከ4 የተጠቀሱትን ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ ማስረጃዎች ይዘው መቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመፈረምና የድርጅቱን አድራሻ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመፈረም ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ22ኛው ቀን እስከ ጧቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በመ/ቤቱ ግዥና ን/አስ/ቡድን ቢሮ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ኦርጂናል ፖስታ እና ኮፒ በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በዚያው በ22ኛው ቀን ጨረታው 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም መ/ቤቱ ጨረታው ይከፈታል።
- የጨረታው መከፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነት በተገለጸላቸው ከአምስት የስራ ቀናት በኋላ ባሉት አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መግባት አለበት።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን የጠ/ዋጋ 1.5% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች ነጠላ ዋጋም ሆነ ጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ፓራፍ ማድረግ አለበት።
- ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ ፀንቶ የመቆያ ጊዜ 30 ቀን መሆኑ ይታወቅ።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደ/ወሎ ዞን የወግዲ ትምህርት ጽ/ቤት