Your cart is currently empty!
ኦሮሚያ ባንክ አ.ማ. ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘዉን ንብረቶች ባሉበት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Oct 29, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የሐራጅ ማስታወቂያ
ኦሮሚያ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘዉን በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
| ተ.ቁ | የተበዳሪው ስም | የንብረት አስያዥ ስም | ለጨረታ የቀረበው ንብረት ዓይነት | አበዳሪው ቅርንጫፍ | ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻና የቦታ ስፋት | የጨረታ መነሻ ዋጋ | የጨረታዉ ቀን፣ ሰዓት እና ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ | ጨረታው የወጣው | ||
| ከተማ፣ ክ/ከ/ ወረዳ/ቀበሌ | የባለቤትነት መረጋገጫ ቁጥር | የቦታ ስፋት በካ.ሜ/ሄክ | ||||||||
| 1 | አቶ ቶሌራ ዱላ ገለታ | ተበዳሪው | የመኖሪያ ቤት | ኩምሳ ሞሮዳ | ኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ ወለጋ ዞን፣ ነቀምቴ ከተማ፣ ጨለለቂ 03 ቀበሌ | 9729/ WLMN/16 | 140 | 3,001,167.83 | በ19/3/2018 ዓ.ም ከ 4፡00-5፡00 ኦሮሚያ ባንክ ኩምሳ ሞሮዳ ቅርንጫፍ ውስጥ | ለመጀመሪያ ጊዜ | 
| 2 | ኒንት አግሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር | ተበዳሪው | መጋዘን | ደራርቱ | ኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ ወለጋ ዞን፣ ጎቡ ሳዮ ወረዳ ጋምቤላ ታሬ ቀበሌ | 605/In-16/2003 | 10.2 ሄክ | 19,092,003.61 | በ19/3/2018 ዓ.ም ከ 4፡00-5፡00 ሰዓት ኦሮሚያ ባንክ ነቀምቴ ቅርንጫፍ ውስጥ | ለመጀመሪያ ጊዜ | 
| 3 | ጋድ ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ/ማህበር | ተበዳሪው | B+G+5 የንግድ ቤት | ቦሌ ሚካኤል | አዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክ/ከተማ | AA000060604125 | 2,668 | 234,705,925.30 | በ19/3/2018 ዓ.ም ከ 3፡00-4፡00 ሰዓት | ለመጀመሪያ ጊዜ | 
| የንግድ ቤት | አዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ | ደ2/9010/13812/004573/02 | 4,761 | 70,956,708.62 | በ19/3/2018 ዓ.ም ከ 4፡00-5፡00 ሰዓት | |||||
| የኢንዱስትሪ ቦታ | አዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ | AA000070700743 | 2,447 | 26,875,063.44 | በ19/3/2018 ዓ.ም ከ5፡00-6፡00 ሰዓት | |||||
የሐራጅ ደንቦች
1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ/ሲ.ፒ.ኦ በኦሮሚያ ባንክ ስም አሰርተው ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል። በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል።
2. ተ.ቁ 3 ላይ ያሉ ንብረቶች ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ቦሌ መንገድ ኦሎምፒያ አካባቢ አምራን ሆቴል ጎን የኦሮሚያ ባንክ የህግ አገልግሎት ቢሮ የሚገኝበት ናትሩት ሀውስ (ህንፃ) 9ኛ ፎቅ ላይ የሚገኝ የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ባለዕዳዎቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይካሄዳል። ባለ ዕዳዎቹ እና ታዛቢዎች ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል።
3. የተጨራቾች ምዝገባ ከሐራጅ መዝግያ ስዓት 5 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል። የጨረታ መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ ከፍተኛ ዋጋ የሰጠ ተጫራች ካልተለየ አስኪለይ ደረስ ጨረታው የሚቀጥል ይሆናል። በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከባንኩ ህግ አገልግሎት ሲደርሰው ብቻ አሽናፊ ይባላል።
4. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች አሸናፊ መሆኑ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ አጠቃሎ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል:: በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ የማያደርግ የጨረታ አሸናፊ ያስያዘው ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል። በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚፈጠረው ልዩነት ይጠየቃል።
5. በባንኩ ብድር ፖሊሲ መሰረት የሚፈለገውን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ ብድር ሊያመቻች ይችላል።
6. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ንብረቱን በማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ግብር፣ የሊዝ ክፍያ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የስም ማዘወሪያ እና ማናቸዉም ከጨረታው ጋር በተገናኘ መንግስት የሚጠይቀው ክፍያ ይከፍላል። ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
7. ውዝፍ የሊዝ ክፍያን በተመለከተ ከእዳ ተመላሽ ብር ካለ ከተመላሽ ብር ላይ የሚከፈል ሲሆን ተመላሽ ብር ከሌለ ግን የንብረቱ ጨረታ አሸናፊ ውዝፍ የሊዝ ክፍያን ሙሉ በሙሉ የሚከፍል ይሆናል።
8. ተጨራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ ለመጎብኘት ይችላሉ።
9. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 557 1372 ወይም 09 11 34 02 75 ዋና መ/ቤት ሕግ አገልግሎት፣ ለተ.ቁ.1 በ057 899 9552 / 057 660 7552 ኦሮሚያ ባንክ ኩምሳ ሞሮዳ ቅርንጫፍ፣ ለተራ ቁ.2 በ057 661 4798/1052 ኦሮሚያ ባንክ ነቀምቴ ቅርንጫፍ ለተራ ቁ.3 በ011-639-2154/70/ ኦሮሚያ ባንክ ቦሌ ሚካኤል ቅርንጫፍ ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
10. ባንኩ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኦሮሚያ ባንክ አ.ማ