Your cart is currently empty!
የቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Addis Zemen(Oct 29, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ተማሪ መታደል ገረመው እና የፍ/ባለዕዳ እነ ወ/ሮ ጋዲሳ ቡሊ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/105572 በጥር 28 ቀን 2016 ዓ/ም በእና የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በ23/04/2017 ዓ/ም የፌ/መ/ ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ/110618 በ13/7/2016 ዓ/ም በ7/05/2017ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት
1ኛ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ክልል ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 550 የሆነው ይዞታ የመለያ ቁጥር AA000021001162 የሆነውን የይዞታ ስፋት 1035 ካ/ሜ በካርታቸው መሰረት ሆኖ ሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 47,351,030 (አርባ ሰባት ሚሊዮን ሦስት መቶ ሃምሳ አንድ ሺህ ሳላሳ ብር) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
2ኛ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ክልል ወስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 011 የሆነ ቤት ይዞታው ሰነድ አልባ መብት ያልተፈጠረለት እና የተነፃፃሪ (ፕሮፖርሽን) ጠቅላላ የይዞታ ስፋት የቀበሌ ቤቶችን ጨምሮ 4289.68 ካ/ሜ መሆኑ ይዞታውና በቀጣይ መብት ሲፈጠርለት በንፅፅር የሚደርሰው የቦታው ስፋቱ የሚደርሰው ድርሻ ተሰልቶ የሚታወቅ መሆኑ ከአጠቃላይ ይዞታው በወንዝ ዳርቻ 707.46 ካ/ም የሚነካው አንዲሁም በመንገድ ጥናቱ መሰረት ድግሞ 368 ካ/ሜ የሚነካው ሲሆን የሐራጅ መነሻ ዋጋ 180,488,296.52 (አንድ መቶ ሰማኒያ ሚሊዮን አራት መቶ ሰማኒያ ስምንት ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ሰድስት ብር 52/100) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 8፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች
የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት