የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen(Oct 29, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ወ/ሮ አለም አጋ እና የፍ/ባለዕዳ አቶ ሳሙኤል ለማ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 173750 በሚያዚያ 21 ቀን 2014 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/201014 በ15/4/2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ፍርድ ለማስፈጸም ይቻል ዘንድ ፍርድ ያረፈበት ቤት በአዲስ አበባ ከተማ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 3 የቤት ቁጥር 425 የካ/ቁ/የካ /207693/10 የሆነ ቤት በካርታው ያለው ይዞታ ስፋት 130 ካ/ሜ ሲሆን በቦታው ላይ የሚገኝው G+2 ቤት አጠቃላይ የቤት ሰፋት 284.78 ካ/ሜ የቤቱ አገልግሎት ለመኖርያ ይዞታው በመንገድ ጥናት 24 ካ/ሜ የሚነካው የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 10,639,120 (አስር ሚሊዮን ስድስት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺህ አንድ መቶ ሀያ ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 22 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

2ኛበየካ ክ/ከተማ ወረዳ 2 የቤት ቁጥር 688 በሆነ ይዞታ ላይ 3 ከፍል ጭቃ ቤቶች በቁጥር የካ/17/001/04 ሴርያል ቁጥር 008175 ስፋቱ 500 ካ/ሜ በአቶ አጋ ገርቢ እና በወ/ሮ ዘነበች አደራ ስም የተመዘገበ ይዞታ ማረጋገጫ ያለው የፍ/ባለመብት እና የፍ/ባለዕዳ በወላጆቻቸው ግቢ ውስጥ በጋራ የሰሩት ውሳኔ ያረፈበት 3 ክፍል ጭቃ ቤት የቤቱ ስፋት 35.28 ካ/ሜ ሲሆን ከግቢው ለቤቱ የሚደርሰው እና ቤቱ ያረፈበት ጠቅላላ 56.50 ካ/ሜ በንፅፅር መሆኑ ይዞታው በወንዝ ዳርቻ (river buttere) ክልል ወስጥ የሚገኝ እና የመንገድ ጥናት የሌለው ፕላን ተቃርኖ መሆኑ የሐራጅ መነሻ ዋጋ 2,058,881(ሁለት ሚሊዮን ሃምሳ ስምንት ሺህ ሰምንት መቶ ሰማኒያ አንድ ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 22 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.RO አሰርቶ በኢትዮያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ እሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *