Your cart is currently empty!
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪከት የቶጎጫሌ መገንጠያ- ጅግጅጋ ኤርፖርት የመንገድ ስራ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 31, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪከት የቶጎጫሌ መገንጠያ– ጅግጅጋ ኤርፖርት የመንገድ ስራ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተዘረዘሩትን የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
| ተ/ቁ | የመሣሪያው ዓይነት | ብዛት | የፈረስ ጉልበት | ስሪት ጊዜ | በሰዓት የኪራይ ዋጋ ነዳጅና ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ | ምርመራ | 
| 1 | ቼን ኤክስካቫተር ባለ ጃካሀመር | 1 | > 170 HP | 
 | 
 | 
 | 
| 2 | ቼን ኤክስካቫተር ባለ አካፋ | 1 | 1.3M3 | 
 | 
 | 
 | 
| 3 | ግራደር | 1 | HP>165 | 
 | 
 | 
 | 
| 4 | ቼን ኤክስካቫተር ባለ ጎማ | 1 | >1M3 | 
 | 
 | 
 | 
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ የኮንስትራክሽን መሳሪያ አከራይ ድርጅት የሆነ ማሟላት ያለባችሁ መስፈርት እንደሚከተለው ይሆናል።
1. የባለቤትነት መታወቂያ/ሊብሬ/ ያለው ወይም ህጋዊ ውክልና፣
2. አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆን ይኖርበታል፣
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት ያለው/ያላት፣
4. የግብር ክፍያ የምስክር ወረቀት፣
5. በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ፣
6. የሶስተኛ ወገን ሽፋን የሚያቀርብ፣
7. ነዳጅ እንዲሁም የጥገና፣ የሾፌር ደሞዝና አበል በአከራይ ይሸፈናል፡፡
8. ከላይ ለተዘረዘሩት የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች በሰዓት የሚከራይበትን ዋጋ ድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ከሚገኘው ቢሮችን በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነድ በመውሰድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት።
9. አሸናፊ ተጫራቾች የቴክኒክ ምርመራውን ካለፈ ውል በመፈፀም ወዲያውኑ ወደ ሥራ መሰማራት አለበት፡፡
10. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ድሬዳዋ በሚገኘው የመ/ቤቱ ዋና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
11. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ዕለት የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብት አለው።
ለበለጠ መረጃ፡–በስልክ ቁጥር 09 27 63 61 26 ደውሎ ማረጋገጥ ይቻላል።
ማሳሰቢያ፡– ብዛትን በሚመለከት እንደ አስፈላጊነቱ ሊጨምር ይችላል።
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪከት