የቦታው ስፋት በካርታቸው መሰረት 129 ካ/ሜ የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen(Oct 31, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ 

የፍ/ባለመብት የፍትህ ሚኒስቴር እና የፍ/ባለዕዳዎች እነ አቶ በኃይሉ መኮንን መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ ቁጥር 138800 በ15/03/2015 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ 158003 በ19/3/2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የሚገኝ በካ/ቁ/ ቦሌ4/19/5/3/9434/30239/01 የሆነ ቤት ካርታ ያለው የቦታው ስፋት በካርታቸው መሰረት 129 ካ/ሜ በባለሙያ ግምት የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 11,108,601 (አስራ አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ አንድ ብር) ሆኖ በመጋቢት 19 ቀን 2017 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል የሚል ማስታወቂያ ወጥቶ በእለቱ ተጫራች አልቀረበም፡፡ ይህንኑ ለፍ/ቤቱ ሪፖርት ተደርጎ ፍ/ቤቱ በ23/7/2017 ዓ.ም በድጋሚ ጨረታ እንዲወጣ ትዕዛዝ የሰጠ በመሆኑ በሁለተኛ ጨረታ የግምቱን 1/4 ኛ ብር 2,777,150.25 (ሁለት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰባ ሰባት ሺህ አንድ መቶ ሃምሳ ብር 25/100) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸ። የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራቾች በሚጫረቱበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ዳ/ ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታው ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *