Your cart is currently empty!
የይዞታው ስፋት 249 ካ.ሜ. የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Addis Zemen(Oct 31, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት አቶ ቢኒያም ጌታቸው እና የፍ/ባለዕዳ አቶ ዳንኤል ክፍሌ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/187461 በ28/9/2015ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/190330 በ13/02/2016 ዓ/ም በ25/10/2016 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 በአቶ ዳንኤል ክፍሌ ስም ሰነድ አልባ ማህደር የተደራጄለት ሰነድ አልባ ቤት የይዞታው ሰፋት 249 ካ/ሜ አዋሰኞች በሰሜን እና በደቡብ መንገድ በምስራቅ አቶ ሙሉጌታ በቃቴ በምዕራብ ወ/ሮ አሰለፈች ከበደ የሚያዋስኑት ቤት የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 8,871,426 (ስምንት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰባ አንድ ሺህ አራት መቶ ሀያ ስድስት ብር) ሆኖ መስከረም 28 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የሚል ማስታወቂያ ወጥቶ በእለቱ ተጫራች አልቀረበም፡፡ ይህንኑ ለፍ/ቤቱ ሪፖርት ተደርጎ ፍ/ቤቱ በ5/2/2018 ዓ/ም በድጋሚ ጨረታ እንዲወጣ ትዕዛዝ የሰጠ በመሆኑ በሁለተኛ ጨረታ የሚያዘው 1/4ኛ ብር 2,217,856.5 (ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ አስራ ሰባት ሺህ ስምንት መቶ ሃምሳ ስድስት ብር) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 22 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍ/ቤት የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት