Your cart is currently empty!
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Addis Zemen(Jan 23, 2026)
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት አቶ ወሂብ ኢድሪስ እና የፍ/ባለዕዳ አቶ ሙኒር አብዱሰላም መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/13206 በ28/11/2017 ዓ/ም በሰጠው ፍርድ እና በኮ/መ/ቁ/20148 በ1/4/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ ዱከም ክ/ከተማ በጎጌቻ ቀበሌ ውስጥ በካርታ ቁጥር lN–016/07 ፕሎት ቁጥር DIS-18 የቦታው ስፋት 2500 ካ.ሜ አገልግሎቱ ለኢንዱስትሪ የሆነ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 6,527,942.25 (ስድስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሀያ ሰባት ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ ሁለት ብር) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ የካቲት 16 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
2ኛ በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ ዱከም ክ/ከተማ የሚገኝ የካርታ ቁጥር 015/07 ዲአይ ኤስ 16 (DIS16) የሆነ ፋብሪካ የይዞታው ስፋት 2,200 ካ/ሜ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 25,692,813.38 (ሀያ አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ዘጠና ሁለት ሺህ ስምንት መቶ አስራ ሦስት ብር 38/100) ሆኖ የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሽጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት