Your cart is currently empty!
የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
Be’kur(Jan 26, 2026)
የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ጎንደር ዞን በፋርጣ ወረዳ የጋሳይ መሪ ማዘጋጃ ቤት የከተማ ቦታን ስለመያዝ በሚደነግገዉ አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንኡስ 1 መስረት በ2018 በጀት አመት 1ኛ ዙር ጨረታ ለመኖሪያ አገልግሎት 5 ቦታዎችን ለድርጅት አገልግሎት 5 ቦታዎችን በድምሩ 10 ቦታዎችን በጨረታ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
- በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛዉም ሰዉ ወይም ድርጅት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛትና መጫረት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት በመንግስት የሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 በመሪ ማዘጋጃ ቤቱ ዉስጥ ይሆናል፡፡
- ጨረታዉ የሚዘጋዉ በ10ኛዉ ቀን ከቀኑ በ11፡00 ነው፡፡
- ጨረታዉ የሚከፈተዉ ማስታወቂያ በወጣ በ11ኛዉ ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 በመንግስት የሥራ ሰዓት ይሆናል።
- ለበለጠ ዝርዝር መረጃ የጨረታ ማስታወቂያዉ ከሚለጠፍበት ቦታዎች ላይ ማየት የሚቻል ሲሆን በስልክ ቁጥር 058 253 01 26 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
የጋሳይ መሪ ማዘጋጃ ቤት