Your cart is currently empty!
በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር የጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽህፈት ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በጨፋ ሮቢት ከተማ ውስጥ የሚገኙ የድርጅት 1400 ካሬ ሜትር የመኖሪያ 2130 ካሬ ሜትር ጠቅላላ ስፋታቸው 3530 ካሬ ሜትር የሆኑ ለድርጅትና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ የልማት ቦታዎችን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል
Addis Zemen(Jan 28, 2026)
የመጀመሪያ ዙር የመሬት ሽያጭ የሊዝ
ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር የጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በጨፋ ሮቢት ከተማ ውስጥ የሚገኙ የድርጅት 1400 ካሬ ሜትር የመኖሪያ 2130 ካሬ ሜትር ጠቅላላ ስፋታቸው 3530 ካሬ ሜትር የሆኑ ለድርጅትና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ የልማት ቦታዎችን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ፡–
1. የጨረታውን ሰነድ በጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ሸያጭ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
2. ተጫራቶች ቦታዎቹ የሚገኙበት ድረስ በመሄድ አጠቃላይ የቦታዎቹን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ።
3. ተጫራቶች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቶች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው ስፔሲፊኬሽን/Specification/ መሰረት መሆን ይኖርበታል።
4. ተጫራቶች በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ቦታ ስፋት በሊዝ መነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 20 በመቶ ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም ከ20 ከመቶ ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል።
5. ተጫራች የጨረታውን ሰነድ፣ ሲፒኦ እና ሌሎች የጨረታ ሰነዶችን በታሸገ ኢንቨሎፕ በአብክመ በኦ/ብ/ዞን በጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከ20/05/2018 እስከ 03/06/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታው የሚዘጋበት ቀን በ03/06/2018 ዓ.ም 11:30 ሰዓት ይሆናል።
7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ04/06/2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት በጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቶች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
8. ቦታውን ለመጎበኘት ለሚፈልጉ ተጫራቶች ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ለሽያጭ የተዘጋጁ ቦታዎች በሚገኙበት የጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ከተማና መ/ል/ጽ/ቤት በሚመድባቸው አስጎብኝዎች ቦታዎቹን መመልከት ይችላሉ።
9. የአካበቢውን ወቅታዊ የሊዝ ጨረታ መነሻ ዋጋ እና ሌሎች የከተማ መሬትን በሊዝ ለማስተዳደር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በማድረግ በጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መመልከት ይችላሉ።
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨረማ ሪመረጃ በስልክ ቁጥር፡– 0919 930 123 / 0910 788 122 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት