የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ፋይናንስ ጽ/ቤት ልዩ ልዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Jan 30, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/2018 ዓ.ም 

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ፋይናንስ /ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 የደንብ ልብስ፤
  • ሎት 2 የፅህፈት ዕቃ፣
  • ሎት 3: የፅዳት ዕቃ፣
  • ሎት 4: ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ፣
  • ሎት 6: የህትመት ዕቃ፤
  • ሎት 7: የድንኳንና ዲኮር መስል ዕቃዎች ኪራይ፤
  • ሎት 8 የመስተንግዶ አገልግሎት፤
  •  ሎት9 የግብርና ዕቃዎች
  • ሎት 10.የመኪና ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ

1. በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው፣ ከአገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣንየዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ፣ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፣የንግድ ስም ምዝገባ ምስክር ወረቀት/ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና በንግድ ሥራ ፍቃድ በጀርባው ያለውን የሥራ ዘርፍ የተገለፀበትን ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

2. በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ እና የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ያካተተ እና የቀረበው ነጠላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ጨምሮ መሆኑን መግለጫ መስጠት አለባቸው

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ማቅረብ የሚችሉ

4. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00ብር /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በለሚ ኩራ /ከተማ ወረዳ 02 //ቤት ሶስተኛ ፎቅ ፋይናንስ /ቤት ከግዥ ክፍል

5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሁሉም ሎት ሃያ ሽህ (20,000) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO)ብቻ ማስያዝ አለባቸው።

6. ተጫራቾች በእያንዳንዱ ዕቃ የሚጫረቱበትን ዋጋ ዝርዝር በመግለፅ በታሸገ ኤንቨሎፕ ያቅራቢ ማህተም እና በዋጋ ማቅረቢያው ዝርዝር ላይ ዝርዝሩን የሞላው ኃላፊ በእያንዳንዱ ዋጋ በተሞላበት የጨረታ ሰነድ ላይ በየገጹ በመፈረም ለዚህ ተብሎ የተዘጋጀውን የጨረታ ሳጥን ውስጥ ኦርጅናልና ኮፒ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ዋጋ ማቅረቢያ ሲያቀርቡ ኦርጅናል ደረጃውን የጠበቀና ናሙናውን ለሚኩራ /ከተማ ወረዳ 02 //ቤት ለግዥ ክፍል ማስረከብ አለባቸው።

8. ተጫራቾች ያሸነፉአቸውን ዕቃዎች ተወዳድረው ካሸነፉ በኋላ ከናሙና ምንም ለውጥ ሳያደርጉ በራሳቸው ወጪ ጭነው የማቅረብና ደረጃውን ያልጠበቀ ዕቃ ከሆነ መልሰው ትክክለኛውን በቀረበው ናሙና መሰረት የማምጣት ግዴታ አለባቸው።

9. ጨረታው የሚዘጋበት በ11ኛው ቀን 400 ላይ ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ፋይናንስ /ቤት ጨረታው ከወጣበት በ11ኛው ቀን 430 ሰዓት ላይ ይሆናል።

10. የጨረታው አሸናፊዎች ማሸነፋቸው በጽሁፍ የሚገለጽላቸው ሲሆን ለጨረታው አፈፃፀም ውል ማስከበሪያ ለአሸነፉበት ዕቃ ዋጋ 10% በማስያዝና ውል የመዋዋል ግዴታ አለባቸው።

11.ናሙና የሚያስፈልጉ እቃዎችን በተባለበት ቀን ውስጥ ማስረከብ አለባችሁ።

12. ክፍያው የሚፈፀመው ለሚያቀርቡት ዕቃ ሙሉ በሙሉ ለፋ//ቤት ንብረት ክፍል ሲያስረክቡና የቀረበው ዕቃ በናሙና መሰረት በጥራቱ ሲረጋገጥ ብቻ ነው።

13. በጨረታ ሰነዱ ላይ የዋጋ ስርዝ ድልዝ እና /ቤቱ የሠጠውን እስፔስፊኬሽን መሰረዝ የለበትም።

14. የጨረታ ማስረከቢያና የውል ማስከበሪያ ደብዳቤ የምታጽፉ ጥቃቅንና አነስተኛ አቅራቢዎች የተሰማራችሁበትን የንግድ ስራ መስክ/ዘርፍ/ የሚገልጽ ደብዳቤ መቅረብ አለበት።

15. ዋስትና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች አሸናፊው ለአመት የሚቆይ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል

16. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ቢበዛ 60 ቀናት ብቻ ነው።

17. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ ስትመልሱ ሙሉ አድራሻችሁን በተሰጠው የመጫረቻ ሰነድ ላይ ትክክል መሙላት ይኖርባችኋል።

18. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡ስልክ ቁጥር +251 11 866 8057 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

ለሚ ኩራ /ከተማ ወረዳ 02 //ቤት ሀያት ወደ ጣፎ የሚወስደው መንገድ ብርሀን ባንክ ያለበት ህንጻ/3ኛ ፎቅ አካባቢው ልዩ ቦታ ክብርዳማና

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር ፋይናንስ /ቤት