ሀና ቅ/አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Jan 31, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 002

ሀና ቅ/አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት እቃዎችን እና ደንብ ልብስ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

1. በዘርፉ የተሰማሩ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የታክስ ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ፣ተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና የገቢዎች ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

ሎት

የቃው/ አገልግሎት አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ

ሎት 1

የጽህፈት ማሳሪያዎች እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች

10,000

ሎት 2

የደንብ ልብስ

5000

ሎት 4

የትምህርት ዕቃዎች

1000

ሎት 5

ቋሚ ዕቃዎች

11,000

2 ተጫራቾች ከዚህ በላይ በሰንጠረዥ በተመለከተው መሰረት በሚወዳደሩበት ሎት ፊት ለፊት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ሀና ቅአንደኛ፣ እንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ስም በማሰራት ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በየሎቱ የማይመለስ ብር 150 አንድ መቶ ሃምሳ ብር በመከፈል ከት/ቤቱ ፋይናንስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በን/ስ/ሳ/ክ/ከ ወረዳ 14 ልዩ ስሙ ሰፈራ ሀና ቅ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 003 በመምጣት የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይቻላሉ።

4. ጥቃቅን እና አነስተኛ ተወዳዳሪዎች አምራች በሆኑበት ዘርፍ ላይ ብቻ ሰነዱን በነፃ መውሰድ ይችላሉ።

5. ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋውን ከነቫቱ ሞልቶና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም አድርጎ ማቅረብ አለበት።

6. የጨረታ ሰነዱ በ10ኛው ቀን ከቀኑ በ11፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን በዓል ካልሆነ ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካያቸው ባሉበት ይከፈታል፣

7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው የጨረታ ሰነድ ኤንቨሎፕ በማሸግ ዋና እና ኮፒ መሆኑን በግልጽ ለይቶ በመፃፍ ማስገባት ይኖርባቸዋል እንዲሁም ናሙና ጨረታ ከመከፈቱ በፊት መቅረብ አለበት፣

8. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ን/ስ/ላ/ክ/ከ/ወረዳ 14 ሰፈራ ታክሲ ተራ ፊት ለፊት ነው።

ስልከ ቁጥር፡- 011 829 0164 / 011 829 0165

በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ የወረዳ 14 ሀና ቅ/አንደኛ፣

አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት