በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የአለታ ወንዶ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


Yedebub Nigat(Jan 31, 2026)

ግልጽ የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ

በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የአለታ ወንዶ አጠቃላይ ሆስፒታል የ2018 በጀት ዓመት የሁለተኛ ግማሽ ዓመት መድሃኒት የህ/መገ መሣ/ሪኤጀንቶችን፣ የተለያዩ ህትመቶችን ፣የእስቴሽነሪ የጽዳት ዕቃዎችን እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ቀጥሎ የተዘረዘሩ ቅድመ ሁኔታዎችንና መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  • የሚፈለገውን የጥራት ደረጃ የሚያሟሉ፣
  • በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  • የዘመኑን ግብር የከፈሉና የ2018 ዓ.ም ፈቃድ ያሳደሱ ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  • በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፣

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚመለስ ብር 10000(አስር ሺህ) በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ የሚችሉ የጨረታውን ዝርዝር የያዘውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00( ሁለት መቶ) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ከአለታ ወንዶ አጠቃላይ ሆስፒታል ከግ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቀርቦ መግዛት ይችላሉ።

ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ብቻ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በግልጽ በመሙላት ቴክኒካልና ፋይናንሻል ኦርጂናልና ኮፒ በተለያዩ ዐ2 (ሁለት) ፖስታ በማድረግ ሁሉንም በአንድ እናት ፖስታ አሽገው ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን እንዲያስገቡ እየገለጸ የጨረታ ሳጥኑ በ15ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት አለታ ወንዶ አጠቃላይ ሆስፒታል በግልጽ ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 046-224-1463/046-224-1461 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በሲዳማ ብ/ክ/መ/ጤና በሮ የአለታ ወንዶ አጠቃላይ ሆስፒታል