Your cart is currently empty!
በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የሰላም ጤና ጣቢያ ለ2018 በጀት ዓመት የ2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ የሚያገለግሉ የተለያዩ ዕቃዎች እና አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Jan 31, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ 002/2018
በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የሰላም ጤና ጣቢያ ለ2018 በጀት ዓመት የ2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ የሚያገለግሉ የጽ/መሣሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የልዩ ልዩ ዕቃዎች፣ መድሃኒቶች፣ ሪኤጀንቶች፣ ሜዲካል ሰፕላይስ፣ ህትመቶች፣ የተለያዩ የጥገና ስራዎች ቋሚ ዕቃዎች የኮምፒውተር ዕቃዎች እና የሠራተኛ የካፊቴሪያ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም የእያንዳንዱን ጨረታ ዝርዝር የያዘ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 31 ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት የማይመለስ ብር በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ለጽህፈት መሣሪያዎች………………………………………ብር 100.00
- ለጽዳት ዕቃዎች……………………………………..….ብር 100.00
- የደንብ ልብስ…………………………………….……..ብር 100.00
- ልዩ ልዩ ዕቃዎች………………………………….………ብር 100.00
- ለመድሃኒት፤ ሪኤጀንትና ሜዲካል ሰፕላይስ………….ብር 100.00
- ለህትመቶች……………………………………………..ብር 100.00
- የተለያዩ የጥገና ስራዎች……………………………..…ብር 100.00
- ቋሚ ዕቃዎች………………………………………….…ብር 100.00
- የኮምፒውተር ዕቃዎች……………………………….…ብር 100.00
- የሰራተኛ ካፌ አገልግሎት……………………………….ብር 100.00
ማሳሰቢያ፤
1. ተጫራቾች የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቾች በየዘርፉ የተወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በ CPO ማስያዝ አለባቸው።
- ለጽህፈት መሣሪያ…………………………………..ብር 1,600.00
- ለጽዳት ዕቃዎች……………………………………….ብር 11,700.00
- የደንብ ልብስ……………………………………ብር 10,950.00
- ለልዩ ልዩ ዕቃዎች…………………………………….ብር 1,600.00
- ለህትመት……………………………………………………..ብር 5,850.00
- ለመድኃኒት ሪኤጀንት እና ሜዲካል ሰፕላይስ…………..ብር 41,300.00
- ለተለያዩ የጥገና ስራዎች………………………….….ብር 1,320.00
- ቋሚ እቃዎች…………………………………………………..ብር 18,150.00
- የኮምፒውተር ዕቃዎች…………………………………………ብር 1,320,00
- የሰራተኛ ካፌ አገልግሎት…………………..…………………..ብር 1,940.00
5. የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል፣
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ከጤና ጣቢያው በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶች ላይ ቫትን ያካተተ መሆኑ መግለጽ ይኖርባቸዋል፣ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ያላደረገ ፣ስርዝ ድልዝ ያደረገ ፣አማራጭ ሳምፕል /ዋጋ/ ያቀረበ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፤
8. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ ናሙና ካላቀረቡ ከውድድር ውጪ ይሆናሉ፣
9. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ ጤና ጣቢያው ንብረት ክፍል ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
10. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በወጣ 10ኛ ቀን 11፡00 ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጤና ጣቢያው ቅጥር ግቢ ውስጥ ይከፈታል፣
11. ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ እና ሰነድ መግዛት የሚችሉት በተሰማሩበት ዘርፍ ብቻ ነው።
12. ጤና ጣቢያው እንደ አስፈላጊነቱ የዕቃውን ብዛት 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ መግዛት ይችላል።
13. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የመጣ የተጫራች ሰነድ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እንገልጻለን።
14. ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡
1. ከእንቁላል ፋብሪካ በላይ በእምቢልታ ሆቴል አስፖልት ከጎማ አደባባይ ከፍ ብሎ።
2. ከጳውሎስ ሆስፒታል አለፍ ብሎ ከጉለሌ ንግድ ባንክ ወደ ወረዳ 9 በሚያስወጣው አስፖልት ከጎማ አደባባይ ከፍ ብሎ
ስልክ ቁጥር 011 259 3899 / 011 259 3900
በጉለሌ ክ/ከተማ ጤና መምሪያ የሰላም ጤና ጣቢያ