በኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የተለያዩ የእርሻ መሳሪያዎችና ተቀጽላ መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 02, 2026)

የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን (የእርሻ መሳሪያዎች አቅርቦትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ) አዲስ አበባ የሚገኙ ከዚህ በታች የተገለጹትን የተለያዩ የእርሻ መሳሪያዎችና ተቀጽላ መሳሪያዎችን በጨረታ ቁጥር: መለዋ/01/2018 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ሎት

የመለዋወጫዎች ዝርዝር

የመለዋወጫዎች ብዛት በአይነት

ሎት 1

የ YTO ትራክተር መለዋወጫዎች

64

ሎት 2

የ IMT ትራክተር መለዋወጫዎች

90

ሎት 3

የ ZT ትራክተር መለዋወጫዎች

364

ሎት 4

የ Bellarus ትራክተር መለዋወጫዎች

213

ሎት 5

የ Combinir (አጭዶ መውቂያ) መለዋወጫዎች

274

ሎት 6

የተለያዩ ባልዲዊን ፊልተሮች

63

ሎት 7

የተለያዩ የእርሻ መሳሪያ ተቀጽላ መለዋወጫዎች

196

ሎት 8

የተለያዩ የጀነሬተር እና Standard መለዋወጫዎች

348

ሎት 9

የተለያዩ ጎማዎች፣ ከመነዳሪዎችና ፍላፖች

12

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።

ሀ) ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እቃዎቹ በሚገኙበት በኮርፖሬሽኑ ዋና ጽ/ቤት አዲስ አበባ በእርሻ መሳሪያዎች አቅርቦት ዘርፍ ሽያጭ ክፍል በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

ለ) የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚካሔደው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ክፍት ይሆናል፡፡ ጨረታውም በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የእርሻ መሳሪያዎች አቅርቦትና ሽያጭ ቢሮ ይከፈታል።

ሐ) ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለጨረታ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 3% በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የእርሻ መሳሪያዎች አቅርቦትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ (Ethiopian Agricultural Businesses Corporation Agricultural Equipment Supply and Mechanization Sector) በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ቃሊቲ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ጽ/ቤት(ሳሪስ አቦ ከፋ ምግብ ኮምፕሌክስ

በስተጀርባ፣ ከደብረዘይት መንገድ 200 ሜትር ገባ ብሎ)

ስልክ ቁጥር 0114-42-25-82, 0114-40-39-70, 0114 42-34-38

የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *