የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የኮንቴነር ግንባታ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 03, 2026)

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት የሚ/አ/ከ/አስ/ር ስራ ከህሎት ጽ/ቤት በባለቤትነት ለሚያሰራው የኮንቲነር ግንባታ ስራ

  • ሎት 1 ኮንቲነር በቁጥር 13
  • ሎት 2 ኮንቲነር በቁጥር 12 በግንባታ ስራ የተደራጁ ማህበራቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላል።

1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።

3. በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።

5. ግብር ስለመክፈላቸው ከገቢዎች መ/ቤት ክሊራንስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

6. የባዮሜትሪክ አሻራ ድጋፍ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

7. የጨረታ ሰነድ ከግዥ ኬዝ ቲም የሥራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን ብር 1000/አንድ ሺ ብር/ ከፍለው በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ።

8. ከአደራጅ መ/ቤት 5 የማህበር አባላት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

9. የጨረታ ሰነዱ ሞልተው ሲመልሱ ቴክኒካሉን 1 ኦርጅናልና 2 ኮፒ ፋይናንሻሉን 1 ኦርጅናልና 2 ኮፒ በሁለት ፖስታ በማድረግ እና በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

10. የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ 30,000/ሰላሳ ሺህ ብር/ ለሎት ሁለት 28,000/ሃያ ስምንት ሺህ ብር/ ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የተረጋገጠ ቼክ፣በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፣ በባንክ የተረጋገጠ ሌተርኦፍ ክሬዲት ለሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በማለት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

11. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ 22ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን በ4፡00 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈትሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።

12. በጨረታው ማስታወቂያ ላይ የትርጉም ስህተት ቢኖር በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፀው ተቀባይነት ይኖረዋል።

13. ሰነዱን ሞልተው ወደ ጨረታ ሳጥን ለማስገባት ሲመጡ ተመዝግበውና ፈርመው ማስገባት አለባቸው።

14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

 


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *