Your cart is currently empty!
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ በግልጽ ጨረታ መሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 03, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ/ከሳሽ እነ ተገኘ በዛብህ እና በአፈ ተከሳሽ አቶ በሪሁን ረብሶ መካከል ስላለው የአፈጻፀም ክርክር ክስ ጉዳይ ፍ/ቤት ጥር 19 ቀን 2018 ዓ ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ መሰረት የአፈ/ተከሳሽ እንደፍርዱ ሊፈጽሙ ባለመቻላቸው ምክንያት በጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ የሚገኘውን በፍ/ባለዕዳ ስም የተመዘገበው የታርጋ ቁጥር ኮድ ኢት 3-14343 የሆነውን ተሸከርካሪ ደረቅ ጭነት መኪና በመነሻ ዋጋ ብር 1,132,942.34 አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሰላሳ ሁለት ሺ ዘጠኝ መቶ አርባ ሁለት ብር ከሰላሳ አራት ሳንቲም በሆነ መነሻ ዋጋ በግልጽ ጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ እዟል።
- የሰሌዳ ቁጥር ኢት 03-14343 የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ
- የሰሪት ሀገር ምዕራብ አውሮፓ /ጣሊያን/
- የተሸከርካሪ ሞዴል 190E31 ፊያት፣ የስሪት ዘመን 1995
- የመጫን አቅም 90.8/ ዘጠና ነጥብ ስምንት ኩንታል+አንድ ሰው
- የሻንሲ ቁጥር WJME3TPT00C061405
- የሞተር ቁጥር 8210-22V-825-430890
- የሚጠቀመው የነዳጅ አይነት ናፍታ
- እንዲከፍል የተወሰነው የብር መጠን 3,951,198.78 ሶስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሃምሳ አንድ ሺ አንድ መቶ ዘጠና ስምንት ከሰባ ስምንት ሳንቲም
በመሆኑም ከላይ የተገለፀውን ተሽከርካሪ መኪና መጫረት (መግዛት) የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ሁሉ የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ መኪናው ከሚገኝበት ቦታ ድረስ በመቅረብ መኪናው አይቶ መጫረት እና መግዛት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች እንድታሟሉ እንገልጻለን።
- ተወዳዳሪዎች በተጠቀሰው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሠዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ መኪናውን አይቶ መቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ግዥ ሲያሸንፍ አንድ አራተኛውን ወዲያውኑ ያስይዛል።
- ገዥ ሲያሸንፍ በ15 ቀን ውስጥ አጠቃሎ ከከፈለ ስመ ንብረቱ ወዲያውኑ እንዲዛወርለት ይደረጋል።
- የጨረታ ተወዳዳሪዎች በጨረታ ወቅት መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በጨረታ የሚወዳደሩ ራሳቸው ወይም ህጋዊ ወኪላቸው ይሆናል።
- በጨረታ ወቅት ሁከት የሚፈጥር በህግ ይጠየቃል።
- ስመ ንብረት ማዛወሪያ በጨረታ አሸናፈው የሚሸፈን ይሆናል።
- ጨረታው በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሐራጅ ባይ የሚመራ ይሆናል።
ከዚህ በላይ በዝርዝር የቀረበውን የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ አሟልታችሁ ለመወዳደር የምትፈልጉ ሁሉ መኪናው ከሚገኝበት በጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ ድረስ በመገኘት መኪናውን በአካል ቀርበው በማየት በጨረታው ቀን እና ሰዓት በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን የማዕ ጎንን ከፍ/ፍ/ቤት እዟል።
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት