በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የቡርጂ ዞን ሶ /ዙ /ወ /ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ ግንባታዎችን ማስገንባት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 04, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር- ET-SOUTH ETH-516154-CW-RFQ
በቡ/ዞ/ዕ/ዙ/ወ/ ት/ት/ጽ/ቤት በቁጥር 1/707/1/25 በ 27/2/2018 በተጻፈ ደብዳቤ

ሎት -1 ደረጃቸው GC ወይም WWC 8 እና በላይ ያላቸውን በረቅ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የሴቶች መጸዳጃ ቤት እና

ሎት 2 አዲስ የሴቶች የንጽህና መጠበቅያ ክፍል/MHMroom/ ደረጃቸው GC ወይም WWC 8 እና በላይ የሆናቸው ተጫራቾችን በመጋበዝ ግንባታ ማስገንባት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች ያለውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን።

በዚሁ መሠረት፡-

1. የእንዱ ነጠላ ዋጋ

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ በዘርፉ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስክር ወረቀት/ቫት/ ብቃት ማረጋገጫ፤ ክሊራንስ እና ሌሎች ሰነዶችን በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስኪወጣ ድረስ ባሉት ሥራ ቀናት እስከ 11፡00 ሰዓት የጨረታውን ሰነድ ከመ/ቤታችን ግን/አስ/ር ዋና የሥራ ሂደት የማይመለስ ብር 1000 / አንድ ሺህ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይቻላል።

4. የሁለቱም ተጫራቾች ጨረታው የሚገባው በ22ኛ ቀን ከጠዋቱ እስከ በ4፡00 ሲሆን የሚከፈተው በዚያው ዕለት ልክ ከጠዋቱ በ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው ወይም የሚመለከታቸው ክፍሎች በተገኙበት ግ/ን/አስ/ር ዋና የሥራ ሂደት ክፍል ይከፈታል ሆኖም 22ኛው ቀን በዓል ወይም ዕረፍት ቀናት ከሆነ በሚቀጥለው ሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፤ ተጫራቾች ፋይናንሻል ኦሪጂናልና ሁለት ኮፒ ቴክኒካል ኦርጂናልና ሁለት ኮፒ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና በሚመለከት ለሁለቱም ለየብቻ ለሴቶች መፀዳጃ ቤት ግንባታ እና የሴቶች ንፅህና መጠበቅያ ቤት ግንባታ ከማናቸው ሕጋዊ ፈቃድ ካላቸው ባንክ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በሌላ /CPO/ ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር የጨረታ ዋስትና የተጠቀሰውን የብር መጠን በጥሬ ገንዘብ ወይም በሌላ /CPO/ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።

6. ተጫራጮች በራሳቸው ትራንስፖርት እስከ ቀበሌ ሄደው ቦታውን ወይም ሳይቱን በማየት የሳይት ምልከታ ደብዳቤ ማቅረብ ግደታ አለባቸው።

7. ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።

8. ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ተጫራቾች አሟልተው የመቅረብ ግዴታ አለባቸው።

9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ጽ/ቤቱ

ለበለጠ መረጃ 09 19 98 62 16 ወይም 09 16 37 65 76
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የቡርጂ ዞን ሶ / ዙ / ወ / ፋይናንስ ጽ / ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *