Your cart is currently empty!
የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
Be’kur(Feb 02, 2026)
የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
የወረታ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታ ስለመያዝ በደነገገው አዋጅ 72/2004/መሠረት በ2018 በጀት ዓመት ለ1ኛ ዙር 1ኛ. ቀበሌ 01 በምስራቅ መንገድ፣ በምዕራብ አማረ መስፍን፤ በሰሜን ወረታ ትሬዲንግ አ/ማ/ር ፣በደቡብ መንገድ፣ ስፋቱ 522 ካ/ሜትር ለድርጅት አገልግሎት የሚውል 01 ቦታ፡፡ 2ኛ. ቀበሌ 01 በምስራቅ መንገድ፣ በምዕራብ መንገድ፤ በሰሜን መንገድ እና አዲሱ፣ በደቡብ ጌቴ ይጅቡ፣ስፋቱ 562.5 ካ/ሜትር ለድርጅት አገልግሎት የሚውል 01 ቦታ፡፡3ኛ. ቀበሌ 03 በምስራቅ ኑርሁ ሴን፣ በምዕራብ ሀብቴ አስካለማርያም፣ በሰሜን መንገድ ፣በደቡብ እንድሪስ፣ስፋቱ 120 ካ/ ሜትር በተራ ቁጥር 03 የተፃፈ ቦታ አሸናፊው 100 በመቶ ክፍያውን መክፈል ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ቢሮ ቁጥር 17 በመምጣት የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
- የጨረታ አይነት መደበኛ፡፡
- የጨረታ ሰነድ መግዣ ቀን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉበት 10 ተከታታይ የስራ ቀን ከጧቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ስዓት ብቻ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነድ መሸጫ ጊዜ የሚያልቀው በ10ኛው ቀን 11፡30 ነው፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ወ/ከ/አስ/ከ/ል/ቤ/ኮ/ጽ/ቤት ከጥዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ሲፒኦ በባንክ የተረጋገጠ የገንዘብ ክፍያ ትዕዛዝ ለድርጅቱ 15 በመቶ ለመኖሪያ 20 በመቶ በማቅረብ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የተያዘ ገንዘብ አሸናፊው ከተለየ በኋላ የሚመለስ ይሆናል፡፡
- የግንባታ ደረጃ ለድርጅት
- የቦታው አገልግሎት በእያንዳንዱ ምድብ ከሰነዱ ጋር በሚሸጠው ሰነድ ሰንጠረዥ ላይ የተቀመጠው ይሆናል፡፡
- ለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 446 00 26 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡
የወረታ ከተማ አስ/ ከተ/ል/ ቤ/ ኮን/ ጽ/ቤት