Your cart is currently empty!
የምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን መሪ ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
Be’kur(Feb 02, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን መሪ ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣
- ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ፣
- ሎት 3 የጽዳት ዕቃ፣
- ሎት 4 የመኪና መለዋወጫ፣
- ሎት 5 የመኪና ጎማ፣
- ሎት 6 የአገር ውስጥ ፈርኒቸር እንዲሁም
- ሎት 7 የውጭ ፈርኒቸር ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሰፈርቶች ማሟላት አለባቸው።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ለሆነ ግዥ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
- ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ ሎት 7 የተዘረዘሩትን እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነድ ምዕራብ ጎንደር ዞን ገ/ውሃ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን መሪ ቢሮ ሶስተኛ ፎቅ ማግኛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በገቢ መሰብሰቢያ ደርሰኝ መሂ 1 በተቆጠረ በጥሬ ገንዘብ ሆኖ የጠቅላላ ግዥውን ዋጋ 2 በመቶ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ የግዥን ዋጋ ገቢ በማድረግ ከፖስታው ውስጥ ማስገባት ወይም በተጫራቾች የሚሞላውን የጨረታ ማስረከቢያ ቅፅ ሞልቶ ማቅረብ አለባቸው፡፡ የጨረታ ሰነዱን ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የመጫረቻ ሰነድ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታውን ለመገምገም በርካታ ጊዜ ለማይወስዱና ውስብስብ ላልሆኑ ግዥች ከአረባ (40) ቀናት መብለጥ እንደሌለበት እያወቁ የመጫረቻ ሰነዱን መሙላት አለብዎት፡፡
- ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ በተጨማሪ ውል እስኪቋረጥ ድረስ ለሚቆይ ሃያ (20) ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅች ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ግዥና ፋይናስ ቡድን መሪ ቢሮ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጥር 25/2018 ዓ.ም እስከ የካቲት 09/2018 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ15 ቀን ቆይቶ የካቲት 10/2018 ከረፋዱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ምዕ/ጎ/ዞ/ ፖሊስ መምሪያ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን መሪ ግቢ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግልጽ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ የሚለየው በሎት ወይም በጥቅል ድምር ስለሆነ የሙሉ እቃ ዋጋ መሙላት አለበት ካልተሟላ ግን ከጨረታ ወጭ የሚሆን መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተቀመጠው የዋጋ መሙያ ፎርም በስተቀር በማሳሰቢያ የሚሞሉ ዋጋ እና የሞዴል መረጃን እንዲሁም የማይነበብ ሥርዝ ድልዝ የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የህዝብ በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ግዥ ፈፃሚ አካል የጨረታ አሸናፊውን በሚመርጥበት ጊዜ መለኪያው ተለይቶ የሚታወቅ እስከሆነ ድረስ በእያንዳንዱ የእቃ መለኪያ የተሰጠውን የነጠላ ዋጋ ወይም ሌሎች የውል ቃሎችና ሁኔታዎችን ሳይለወጡ የዕቃውን ብዛት ወይም መጠን እሰከ 20 በመቶ ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት የውል ማስከበሪያ የሞላውን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንት ወይም (ሲፒኦ) በማስያዝ በምዕ/ጎ/ዞ/ዐቃቢ ህግ መምሪያ በመቅረብ ውል መውሰድ የሚችል ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ሆኖም የምክንያቶቹን አግባብነት እንዲያስረዳ አይገደድም፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 058 331 08 83 /09 18 23 70 63 /09 08 25 18 46 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ
cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx House Furniture cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Office Furniture cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Spare Parts and Car Decoration Materials cttx, cttx Stationery cttx, cttx Wood and Wood Working cttx, Electromechanical and Electronics cttx