የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለ2018/2019 የምርት ዘመን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ውል ከተፈፀመበት ቀን እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 04, 2026)

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 76/2018

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለ2018/2019 የምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል አፈር ማዳበሪያ 79,046.00 (ሰባ ዘጠኝ ሺህ አርባ ስድስት ኩንታል) ቀበሌ ገበሬ መሠረታዊ ማኅበራት መጋዘን ድረስ ለማጓጓዝ ብቃት ያላቸውን የትራንስፖርት ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ውል ከተፈፀመበት ቀን እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል። ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎች፣

የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ግብርና መምሪያ ለ2018/2019 የምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል አፈር ማዳበሪያ ለማጓጓዝ ብቃት ያላቸውን የትራንስፖርት ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ውል ከተፈፀመበት ቀን እስከ ሰኔ 30 ቀን 208 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎች፡-

  1.  የታደሰ ንግድ ሥራ ፊቃድና የዘመኑ የመንግሥት ግብር ስለመከፈሉ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ግዴታ መሆኑ፣
  2. የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት /ቲን/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
  3. በዘመኑ የታደሠ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
  4. የተሽከርካሪ ዝርዝር ተ.ቁ፣ የሰሌዳ ቁጥር፣ የመኪናው ዓይነትና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ከፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ወይም ከክልል መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ የተሰጠ የ2018 ዓ.ም ወቅታዊ የታደሠ ምዝገባ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ 1 እስከ 4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው
  6. የሚጓጓዘውን የአፈር ማዳበሪያ አይነት፣ መጠን እና ቦታ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ 80000 (ሰማኒያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ በደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ስም በመክፈል የተከፈለበትን ደረሰኝ ከሰነዱ ጋር አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሠነዱን በአንድ ፖስታ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በማሸግ በደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ይውላል። ይህም እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በዚህም ሰዓት ይታሸጋል። 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች የውስጥ ኦዲተሮች በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች ከተጠቀሰው ጊዜ ቀድመው የጨረታ ሰነዱን ካስገቡ የመጨረሻ ቀኑን ሳይጠብቅ ለሁሉም ተጫራቾች በደብዳቤ በመጥራት ጨረታው ይከፈታል። ተጫራቾች በአከፋፈቱ ሥነሥርዓት ላይ ባለመገኘታቸዉ የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም።
  9. መሥሪያ ቤቱ የሚያወዳድረው ለአንድ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ለአንድ ኩንታል በሚያቀርበው ነጠላ ዋጋ ነው
  10. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ _ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር ı ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0116375610 በመደወል ማግኘት ይቻላል።

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *