የምዕራፍ አጠቃላይ ደረጃ ትምህርት ቤት የትምህርት መገልገያ እና የቢሮ መሳሪያዎችን በ3ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 05, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 003/2018

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የምዕራፍ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ከመደበኛ በጀት እና ከውስጥገቢ በጀት በመንግስት ግዥ መመርያ መሰረት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የትምህርት መገልገያ እና የቢሮ መሳሪያዎችን በ3ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ ) በመክፈል የምዕራፍ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግዢ ቢሮ ቁጥር 12 መውሰድ ትችላላችሁ፡፡

ተ.ቁ

የእቃው አይነት

ሎት

የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ( CPO )

1

የፅህፈት የት/ት እና የቢሮ እቃዎች

1

2198.47

2

የፅዳት እቃዎች

2

1804.94

3

ደንብ ልብስ

3

750.00

4

ልዩ ልዩ እቃዎች

4

262.34

5

የቤተ-ሙከራ እና የላብራቶሪ

5

1000.00

6

ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች

6

940.00

7

የህትመት ውጤቶች

7

123.00

8

የህክምና እቃዎች

8

393.00

9

የታሸገ ውሀ እና ቆሎ

8

250.00

 ማሳሰቢያ

  1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል እና የዘመኑን ግብር የከፈለ፡፡
  2. በዘርፉ የተሰማሩበት ንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. አቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
  4. የቫት ተመዝጋቢ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ ቫትን ጨምሮ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅራቢያ ቦታ በግልፅ ማስፈር እና መጨረሻ ቦታ ላይ ፊርማ እና ማህተም በመምታት በ1 ኦርጅናል እና 1 ኮፒ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ የሆነባቸውን እቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10 ፐርሰንት የውል ማስከበርያ በማስያዝ እና የግዥ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል ፡፡
  7. አሸናፊው ድርጅት የትራንስፖርት ወጭ በራሳቸው እስከ ት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታ የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በወጣበት 10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 15 ይከፈታል፡፡
  10. እያንዳንዱ ተጫራች የዕቃዎችን ናሙና /ሳምፕል/ የጨረታው ሰነድ ሲገባ (ጨረታው ከመከፈቱ በፊት) ማቅረብ አለባቸው፡፡
  11. የውል ማስከበርያም ሆነ የጨረታ ማስከበርያ ብር በጥሬ ገንዘብ የማንቀበል መሆኑን እየገለፅን በባንክ የተረጋጋጠ ሲፒኦ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ትምህርት ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ የእቃውን መጠን ከውል በፊት 20% መጨመር እና 20% የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  13. ተጫራቾች በጥቃቅን እና አነስተኛ ፍቃድ የምትወዳደሩ ከሆነ አምራቾች ባመረቱት ምርት (ተጨማሪ እሴት)ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡ በዚሁ መሰረት ልዩ አስተያየት የሚደረግላቸው መሆኑን አየገለፅን ከአደራጅ ተቋም ይህን የሚገልፅ የድጋፍ ደብዳቤ እንድታቀርቡ እንጠይቃለን፡፡
  14.  ትምህርት ቤቱ የተሸለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ – አዲስ አበባ ጉስሴ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አንበሳ ጋራዥ በስተጀርባ ወይም ከዊንጌት ወደ አዲሱ ገበያ በሚወስደው መንገድ በስተቀኝ ከፖሊስ ካምፕ ከፍ ብሎ የምዕራፍ አጠቃላይ /2ኛ ደረጃ ት/ቤት ወይም ከአዲሱ ገበያ ዊንጌት በሚወስደው መንገድ በስተግራ በኩል ዜብራ መንገድ ተሻግሮ ከጄኔራል ታደሰ ብሩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ዝቅ ብሎ ባስው ቀጭን መንገድ ገባ ብሎ ወደ ቀኝ ታጥፎ የምዕራፍ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በሮ ቁጥር 12፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-2595671 አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ ጉለሌ

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ስር የሚገኘው

የምዕራፍ አጠቃላይ ደረጃ ት/ቤት