Your cart is currently empty!
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ህዳሴ የመ/ደ/ት/ቤት የጽዳትና የደንብ ልብሶች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ሕትመት እና ልዩ ልዩ መሣሪያዎችና መጽሐፍት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 06, 2026)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ሁለተኛ ጨረታ ቁጥር 002/18
በኮልፌ ቀራንዮ ከፍለ ከተማ ወረዳ 02 ህዳሴ የመ/ደ/ት/ቤት በ2018ዓ.ም የሥራ ዘመን የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁስ ማለትም
- ሎት 1 የጽዳትና የደንብ ልብሶች
- ሎት2. አላቂ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 3 ሕትመት
- ሎት 4 ልዩ ልዩ መሣሪያዎችና መጽሐፍት
የመሳሰሉትን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት / ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሰነድ ማስረጃዎችን ዋናውንና ኮፒ ማቅረብ አለባቸው
- ተጫራቾች የተዘረዘሩትን እቃዎች ናሙና ማቅረብ የሚችሉ ቋሚ እቃዎች ገዢው ት/ቤት በአካል መጥቶ ለማየት ከፈለገ ለመተባበር ፍቃደኛ ሊሆኑ የሚችሉ መሆን አለበት።
- ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ካራቆሬ ከሚገኘው የኮልፌ ቀራንዮ ከፍለ ከተማ ወረዳ 02 በሚገኘው የህዳሴ የመ/ደ/ት/ቤት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ተከታታይ የሥራ ቀናት በመቅረብ ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2:30-11:30 ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ በት/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀን ከ 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት በት/ቤቱ ግዢ ቢሮ ሰነድ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ11ኛው ቀን 4 ሰዓት ታሽጎ 4፡30ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ት/ቤቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፊ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከቫት ጋር መሆን አለበት።
- ጥቃቅንና አነስተኛ የሚያመጡት ደብዳቤ በጽ/ቤት ኃላፊ የተፈረመ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 2000 እና ለሎት 2 ብር 3000 ለሎት 3 ብር 1000 ለሎት 4 ብር 2000 የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ /cpo/ በተረጋገጠ ቼክ በመሥሪያ ቤታችን ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃ በሙሉ ለትምህርት ቤቱ ንብረት ክፍል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- የቋሚ እቃዎችን መሥሪያ ቤቱ ድረስ ሳምፕል ማምጣት የማይችሉትን በፎቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
አድራሻ፡- ልዩ ቦታው ካራ ቆሬ
ኮንደሚኒየም ወይም ቢቂላ መናፈሻ ጀርባ
ስልክ ቁጥር 0912120394 /093777 6785
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ህዳሴ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
cttx Advertising and Promotion cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Education and Training cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Hand Tools and Workshop Equipment cttx, cttx Materials cttx, cttx Mechanical cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Printed Advertising Materials cttx, cttx Printing and Publishing cttx, cttx Promotional Items cttx, cttx Raw materials cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Stationery cttx, cttx Textile, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx