የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 07, 2026)

የተሽከርካሪዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር LAMC/BD/06-06/2018

የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መመዘኛዎች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ግሎባል በሚገኘው ከንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ጀርባ ባለው የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ በሚገኘው ቢሮ ቁጥር 10 በመምጣት የንብረቶችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፣

2. ተሽከርካሪዎቹ የሚገኙበት አድራሻ ግሎባል በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ግቢዎች እና ሳሪስ በሚገኘው የጥቁር ዓባይ አክስዮን ማኅበር ግቢ ውስጥ ነው፡፡

3. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ተሽከርካሪዎቹን በተራ ቁጥር 2 ላይ በተጠቀሰው ቦታ /አድራሻ/ በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣

4. ተሽከርካሪው ቀደም ሲል ያልተከፈለ የቦሎ እና የጉምሩክ ቀረጥ ግብር ወጪ ካለው ባለንብረቱ መሥሪያ ቤት የሚሸፍን ሲሆን የስም ማዛወሪያ፣ የትራንዚት እና ሌሎች ወጪዎች ግን በገዥው ይሸፈናል፣

5. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረቶች የጨረታ መነሻ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 10 ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5. ጨረታው የካቲት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፣

6. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ይደረጋል፣

7. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው፡፡

8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፤

9.ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0942-52-36-99/0912-13-47-91 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣

10. ኮርፖሬሽኑ በማናቸውም ጊዜ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን
አዲስ አበባ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *