Your cart is currently empty!
የጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል የቢሮ አላቂ ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ ልዩ ልዩ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና አመታዊ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የእሳት አደጋ ሲሊንደር ድራይም ፖውደር ሙሌት እና የዴይኬር ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 07, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግልጽ ጨረታ ቁጥር 07/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ የተለያዩ ሎቶችን የሚሆኑ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ ከገቢዎች በጨረታ እንዲሳተፋ የተገለፀበት ደብዳቤ ያላቸው እና በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የሚገልጽ ማስረጃ እና በዘርፉ የተሰማሩ የማይመለስ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው። በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው ሰነድ በነፃ ለሚወስዱ ማህበራት በዘርፉ ስለመደራጀታቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ከላይ የተዘረዘሩ የእቃ ወይም አገልግሎት አይነቶች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በሆስፒታሉ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድረስ በአካል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በድርጅቱ ስም ከድርጅቱ አካውንት ተዘጋጅቶ የሚቀርብ
- ሎት 1፡- የቢሮ አላቂ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺ ብር)
- ሎት 2፡- የጽዳት ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር)
- ሎት 3፡- የደንብ ልብስ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺ ብር)
- ሎት 4፦ ልዩ ልዩ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺ ብር)
- ሎት 5፦. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና አመታዊ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺ ብር)
- ሎት 6፡- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺ ብር)
- ሎት 7፡- የእሳት አደጋ ሲሊንደር ድራይም ፖውደር ሙሌት የጨረታ ማሰከበሪያ ብር 5,000.00 (አምስት ሺ ብር)
- ሎት 8፡- የዴይኬር ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO “ለጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል” ተብሎ በማዘጋጀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተዘጋጀው ዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ላይ ብቻ በመሙላት የድርጅታቸውን ማኀተምና ፊርማ አኑረው ፋይናሻል ኮፒ 1፣ ቴክኒካል ኮፒ 1፣ ፋይናሺያል ኦርጅናል 1 እና ቴክኒካል ኦርጅናል 1 በድምሩ 4 ፖስታ በማድረግ ዘወትር በስራ ቀንና ሰአት ከጠዋቱ 2፡30 – 11፡30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል። ተጫራቾች በራሳቸው ፈቃድ ባይገኙ ጨረታው ከመከፈት አያግደውም፡፡11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
- ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል እንዲሁም ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
- አሸናፊ ተጫራች አሸናፊ የሆነባቸውን እቃዎች ያለምንም አቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የእቃ ከምችት ያለውና የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10% ለውል ማስከበሪያነት አስይዞ ተገቢውን ውል በመፈጸም እቃዎቹን በሆስፒታሉ ግቢ ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ አለበት።
- ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ወይም ልዩ ስሙ ጥምቀተ ባህር ወይም
አቃቂ መሿለኪያ ፊት ስፌት ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 09 24 77 78 40 በስራ ሰዓት ብቻ መደወል ይችላል።
የጥሩነሽ ቢጂንግ አጠቃላይ ሆፒታል
cttx Carpets and Curtains cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Education and Training cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Equipment cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx Hand Tools and Workshop Equipment cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Maintenance and Repair cttx, cttx Materials cttx, cttx Mechanical cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Machines and Computers cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Others cttx, cttx Plastic Products cttx, cttx Plastic Raw Materials and Products cttx, cttx Safety and Security cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Stationery cttx, cttx Textile, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx